www.maledatimes.com ሐሰተኛ ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት የፈጸሙ 124 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሐሰተኛ ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት የፈጸሙ 124 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ

By   /   November 10, 2018  /   Comments Off on ሐሰተኛ ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት የፈጸሙ 124 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second

ሐሰተኛ ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት የፈጸሙ 124 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ

ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል 

9 November 2018ብርሃኑ ፈቃደ( The reporter)

ትክክለኛ ማንነታቸውና አድራሻቸውን ሆነ ብለው በሐሰተኛ ሰነዶች በመሰወርና ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ተግባር እጅ ከፍንጅ የተያዙትን ጨምሮ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ሲፈጽሙ የነበሩ 124 ሐሰተኛ ድርጅቶች መያዛቸውን አዲሱ የገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

በሚኒስቴሩ የሕግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘውዴ ተፈራ ረፋዱን ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ሐሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ፣ በሐሰተኛ ንግድ ፈቃድ፣ በሐሰተኛ የንግድ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በሐሰተኛ የንግድ አድራሻ ከገቢዎች ዕይታና ክትትል ውጭ በሆነ መንገድ ደረሰኝ እጅ በእጅ ሲሸጡ የነበሩትን ጨምሮ በሌሎችም ነጋዴዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ መንገድ ደረሰኝ እየገዙ ወጪያቸውን በማናር ገቢ አሳንሰው የሚያቀርቡና ደረሰኞቹን በመግዛት በተባበሩና ወንጀል በፈጸሙትም ላይ ክትትልና ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

በሐሰተኛ ደረሰኝ ግብይት መበራክት ሳቢያም ሚኒስቴሩ መሰብሰብ ከሚጠበቅበት የሦስት ወራት ግብር ውስጥ 3.1 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንዳልቻለ ተጠቅሷል።

ደረሰኞቹ በኮሚሽን በሕገወጥ ደላሎች አማካይነት እንደሚሸጡ ደርሰንባቸዋል ያሉት አቶ ዘውዴ፣  “ጉዳዩን ለማረጋገጥ ደረሰኝ በደላላ አማካይነት ገዝተን እጅ ከፍንጅ ይዘናቸዋል፤” ካሉ በኋላ በዚህ ሥራ በስፋት የሚሳተፉት ከቀረጥ ነፃ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች፣ ብረታ ብረትና ሌሎችም ዕቃዎችን በማስገባት ከታለመላቸው ዓላማ ውጭ ለመሸጥ በሚደረግ ሙከራ ጭምር ነው።

በሥጋት መጠናቸው በከፍተኛ፣ መካከለኛን ዝቅተኛ ደረጃ የተለዩ ግብር ከፋዮች እንዳሉ የጠቀሱት አቶ ዘውዴ፣ “ስለምናውቃችሁ ተጠንቅቁ ብለናቸዋል”በማለት ከፍተኛ የሥጋት ቀለበት ውስጥ የሚገኙ ግብር ከፋዮች በስም ዝርዝር ተለይተው ኦዲት እንደሚደረጉና ማስጠንቀቂያውም እንዲደርሳቸው መደረጉን አስታውቀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on November 10, 2018
  • By:
  • Last Modified: November 10, 2018 @ 11:52 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar