ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአሁኑ ሰዓት መግለጫ እየሰጠ ሲሆን፤ በእስካሁኑ መግለጫም ተከታዮቹ ነጥቦች ተነስተዋል-
ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘ ላላፉት አመታት በርካታ ጥሰቶች ተፈጽሟል ብሏል፤
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች ያሉት ወንጀሎች መፈጸማቸው በምርመራ ተለይቷል ነው ያለው፤
• በህግ የማይታወቁ ስውር እስር ቤቶች ነበሩ፤ በአዲስ አበባ ሰባት ቦታዎች በሌሎችም እንዲሁ ተገኝተዋል፤
• በሽብር ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎች በድብቅ እስር ቤት ይታሰሩ ነበር፤ ምክንያቱም በድብደባ ወንጀሉን ለማሳመን ነበር፤
• ተጠርጣሪዎችም ስለመታሰራቸው ማንም እንዳያውቅ ይደረግ ነበር፤
• የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተገድደው ከፓርቲ አበልነታቸው እንዲወጡ ይገደዱ ነበር፤ እንቢ ካሉ ይደበደቡ ነበር፤
• የተለያዩ የጦር መሳሪዎችንና ሰነዶችን ተጠርጣሪዎች የእኔ ነው ብለው እንዲፈርሙ ማስገደድ ነበር፤
• ፖሊስ ጣቢያ፣ ማረሚያቤት እና ስውር እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በአሌክትሪንክ ሾክ ማድረግ፣ ብልትን በፒንሳ መሳብ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ ለረጅክ ጊዜ ማቆየት፣ ጫካ ውስጥ ርቃንን ማሳደር፣ ጥፍር መንቀል፣ በብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ አይናቸው ከታሰረ በኋላ ከከተማ አውጠቶ ጫካ ውስጥ መጣል፣ አልፎ አልፎ ከአውሬ ጋር በማሰር ማሰቃየት ሲደረግ ነበር፤
• በዚህ አይነቱ ስቃይ የተነሳ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ የስነ ልቦና ጉዳይት የደረሰባቸው ዜጎች አሉ፤ ይሄን የሚያሳይ ሰነድና የሰው ምስክር አለ፤
• ከዚህ ሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ 36 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውለናል፤
• በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ላይ በተደረገው ምርመራም በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ግዥዎቹ እና በህዳሴው ግድብ ላይ ማጣራት ተደርጓል፤
• ሜቴክ ውስጥ ከህግ ውጭ የተፈጸሙ ግዥዎች፤ በዝምድና የተሳሰሩ ግሰለቦች የፈጸሙት ግዥ መኖሩ ታውቋል
• ሜቴክ ከ2004 -2010 ዓም ድረስ የ37 ቢሊዮን ብር ግዥ ያለምንም ጨረታ ፈጽሟል፤
• የተፈጸሙት ግዥዎች በደላላ የተፈጸሙ ናቸው፤ ደላላዎቹም ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ናቸው፤
• በድለላና በተለያዩ መልኩ የተሳተፉ ግለሰቦች በአገር ውስጥ ያፈሩት ሀብት እንዳለ ሆኖ ከአገር ውስጥ ያሸሹትም አላቸው፤
• ሜቴክ ከአንድ ተቋም ጋር ተዳገጋሚ ግዥ ይፈጽማል፤
• ከውጭ አገር ተገዝቶ በጉሙሩክ እንዳያልፍ በሱዳን በኩል የገባ የግንባታ መሳሪያ አለ፤ ይህ መሳሪያ አሁንም ድረስ በግለሰብ እጅ ያለ ነው፤
• በአገር ውስጥ ግዥም አጋር ናቸው በማለት ከኮርፖሬሽኑ ጋር ዝምድና ካላቸው ሰዎች ላይ ግዥ ሲፈጸም ቆይቷል፤
• ከአንደ ድርጅት ለ21 ጊዜ ከሌላ ድርጅት 15 ጊዜ፣ 18 ጊዜ … ተደጋጋሚ ግዥዎች ተፈጽመዋል፤
• ለአብነት ያህል ከአንድ ድርጅት ብቻ የ205 ቢሊዮን ብር ግዥ ያለጨረታ ተፈጽሟል፤
እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት በጥቅሉ 126 አካባቢ ናቸው፡፡ ከእነዚህም 63 በሽብር ድርጊት፣ 27 በሙስና፣ 36 ደግሞ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ናቸው። ሊብሬ፣ የአክስዮን ደብተር፣ የቤት ሽያጭ ውሎች፣ ጦር መሳሪያዎች ወዘተ በኤግዚብትነት ተይዘዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህጉ <<አሁንም የምንጠረጥራቸው ነገር ግን በሃገር ውስጥና በውጪ ተሸሽገው ያሉ አሉ። በውጪ ያሉትን መንግስታቶቹ አሳልፈው እንዲሰጡን በመነጋገር ላይ ነን። ሀገር ውስጥ ያሉት ደግሞ ራሳቸውን ወደ ሕግ እንዲያቀርቡ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ የፍትህ ሂደታቸውን እንዲከታተሉ ጥሪ እናቀርባለን>> ብለዋል ።
Average Rating