www.maledatimes.com ✍🏽 በ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የተደረገ ምርመራ እና መግለጫ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

✍🏽 በ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የተደረገ ምርመራ እና መግለጫ

By   /   November 14, 2018  /   Comments Off on ✍🏽 በ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የተደረገ ምርመራ እና መግለጫ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 5 Second

✍🏽 በ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የተደረገ ምርመራ እና መግለጫ

– ANA (All Nippon Airways) የተባለዉ የጃፓን አየር መንገድ ከቦይንግ ያዘዛቸዉ 5 B787 ድሪም ላይነር ደረጃቸዉን ያልጠበቁ በመሆኑ እና ዲዛይናቸዉ ችግር ስላለበት እንዲሁም ጭነት ሳይጭኑ በራሱ ከባድ በመሆናቸዉ ከቦይንግ ጋር የነበረዉን ዉል ያፈርሳል፡፡ ቦይንግ ገዢ እንደምንም ሲያፈላልግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፈቃደኛ በመሆን ይወስዳቸዋል፡፡አየር መንገዱ 5ቱን አዉሮፕላኖች እያንዳንዱን አዉሮፕላን በ 90 ሚሊየን ዶላር ከገዛ በኋላ መልሶ ለደቡብ አሜሪካ አንድ ካምፓኒ እያንዳንዱን በ 120 ሚሊየን ዶላር ይሸጥለታል፡፡ ይህ ካምፓኒ ከገዛቸዉ በኋላ መልሶ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በ 25 አመት ዉል ያከራየዋል፡፡ ያ ማለት አሩሮፕላኖች እስኪያረጁ ማለት ነዉ፡፡በዚህ ዉል ላይ ከ 15 ሚሊየን ዶላር በላይ ኮሚሽን ለአየር መንገዱ ሃላፊዎች ተከፍሏል፡፡

– እኒህ በሊዝ ተከራይቶ የሚያበራቸዉ አዉሮፕላኖች የሞተር ዘይት ችግር ምክንያት እንዲሁም የተገጠመለት Rolls-Royce Trent 1000 ሞተር ችግር ምክንያት 4ቱ አዉሮፕላኖች ከአመት በላይ ሳይበሩ ተቀምጠዋል፡፡ የዚህ አውሮፕላን የሊዝ ክፍያ በዶላር በወር 800,000 እስከ 1.25 ሚሊየን USD ድረስ ነው፡፡ ሳየሰሩ በየወሩ መንግስት 1.25 ሚሊየን ዶላር ለደቡብ አሜሪካዉ ካምፓኒ ይከፍላል ማለት ነዉ፡፡አየር መንገዱ ደግሞ በቀን የሚያስገባዉን እስከ 110 ሽህ ዶላር ያጣል፡፡
– የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊዉ የግሉ አዉሮፕላን እንዳለዉ ተረጋግጧል (ከክንፈ ዳኛዉ ጋር በሸር የገዟት ናት ይባላል)፡፡ አዉሮፕላኗ የተመዘገበችዉ Boeing 767-300 ER ET AMF በሚል ነዉ፡፡ አዉሮፕላኗ ባብዛኘዉ ግብጽ እና ታንዛኒያ ትበራለች፡፡ አቶ ተወልደ በሲሸልስ የ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ያስገነባ ሲሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የፕሮሞሽን ክፍል ዉስጥ ሲሸልስ የሚሄዱ ፓይለቶች እና ሌሎች ሰራተኞች ይሄን ሆቴል እንዲጠቀሙ ይገፋፋሉ፡፡ የህወሃት እና የሜቴክ ሃላፊወች የቅዳሜ እና እሁድ የሚያሳልፉት ሲሸልስ በዚህ ሆቴል ዉስጥ ነዉ፡፡
– በዉጭ ሀገር ባሉ የአየር መንገዱ የቲኬት መሸጫወች የተሰበሰበ 67 ሚሊየን ዶላር ወደ ሃገር ቤት ሳይገባ በዛዉ ቀርቷል፡፡ በተጨማሪም በዶላር ለሃገሪቱ ገቢ መደረግ የነበረበት 85 ሚሊየን ዶላር እዛዉ ዉጭ ሃገር በግለሰቦች ባንክ በማስቀረት ከሜቴክ እና ወጋገን ባንክ በወጣ የኢትዮጵያ ብር ገቢ ተደርጓል፡፡

– የአየር መንገዱ ሃላፊ ሰራተኞችን በዘር እና በዘምድ አዝማድ በመቅጠር እንዲሁም በማባረር ተጠምዶ ከርሟል፡፡ ሁለተኛ ሚስቱን በሎስ አንጀለስ የአየር መንገዱ ጣቢያ ሃላፊ አድርጎ ሹሟል፡፡ቦርድ ሳይፈቅድለት የአየር መንገዱ ሃላፊ በየ ሁለት ወሩ ጀርመን የህክምና ክትትል ያደርጋል፡፡ ይህም በሚሊየን ዶላር ወጭ አስወጥቷል፡፡
– በባለፈዉ አመት በማኔጅመንት ችግር 450 አካባቢ የበረራ አስተናጋጆች፤ 80 ቴክንሺያኖች፤ አብራሪዎች እና ሌሎች በመቶወች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ለቀዋል ወይም በብሄራቸዉ ምክንያት ተባረዋል፡፡
– ክነፈ ዳኛዉ እና ተወልደ ሁነዉ ሜቴክ የገዛትን አዉሮፕላን ለሌላ ድርጅት (ኤሽያ ኔፓል ዉስጥ ላለ የእርዳታ ድርጅት ነዉ የሚል ሲሆን መረጃዉ በደንብ ስላልተረጋገጠ ቀጣይ ይጣራል) አከራይተዋታል፡፡ አገናኙ ተወልደ ነዉ፡፡
– የአየር መንገዱ ሃላፊ ተወልድ በዘመዱ በአዲያም ገብረእግብሄር ስም 4 የተለያዩ ህንጻወች አዲስ አባባ ዉስጥ እያስገነባ እንደሆነ ተደርሶበታል፡፡ አዲያም ገብረእግዛብሄር የሳሙኤል ሰንሻይን ባለቤት ዉሽማ ስትሆን ህንጻዉቹ የሚሰሩት በሰን ሻይን ኮንስትራክሽን ነዉ፡፡ አዲያም ገብረ እግዛብሄር የኢትዮያን ካር ጎ በመጠቀም ዘመናዊ መኪናወችን ያለቀረጥ ከጀርመን በማስገባት እና በመሸጥ ትታወቃለች፡፡

– ለሰራተኞች መኖሪያ ብሎ አየር መንገዱ ያሰራዉ ህንጻወች ለአንድ ብሄር ልጆች ብቻ በመስጠት እንዲሁም ህንጻወችን ለመስራት ጨረታ ያሸነፈዉን ድርጅት በመተዉ ለአንድ ለህወሃት ካምፓኒ (አፍሮ ጺወን) በመስጥት በሚሊየን የሚቆጠር ብር ጠፍቷል፡፡
– የአየር መንገዱ የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ባልተቤት የአየር መንገዱ ሰራተኛ ሳይሆን ከአየር መንገዱ ደሞዝ ይወስዳል፡፡
– የአየር መንገዱ የዲጅታል ዲፓርትመንት የፖለቲካ ማስኬጃ በማድረግ ከ 120 በላይ የአይ ቲ ባለሙያቸወን በመቅጠር ሶሻል ሚዲያን በመጠቀም ህዝበን ከህዝብ ሲያጋጩ ይዉላሉ፡፡ ሰሞኑን ሊታወቅ ይችላል ተብሎ በመፍራት ወደ 60 ሚሆኑትን ቀንሰዋል፡፡
– አየር መንገዱ ለድራግ እንዲሁም የዝሆን ቀንድ እና የከበሩ ማእድናት ኢሌጋል ቢዝነስ ዉስጥ በመግባቱ ብዙ ሀገሮች ማስጠንቀቂያ ለአየር መንገዱ ሰተዋል፡፡
– ለሰራተኞች መኖሪያ መገንቢያ ገንዘብ ከ PTA ባንክ በሚሊየን ዶላር ተበድሮ ነገር ግን ግማሹ ቤቱ ሳይሰራ የት እንደደረሰ አይታወቅም፡፡
– 2.4 ሚሊየን ብር ለሃጂ ተጓዦች ለተጉላሉበት ሆቴል እና ምግብ ተብሎ ወቶ የአየር መንገዱ ሃላፊዎች ተከፋፍለዉታል፡፡ ይህ የሆነዉ የሃጂ ተጓዦች አየር መንገዱ ዉስጥ ያለምግብ እና መኝታ ለብዙ ቀን እየተጉላሉ ነበር፡፡
– አየር መንገዱ የሚያሰራዉ ሆቴል ኦዲት ሲደረግ እጅግ ብዙ ገንዘብ የፈጀ ሲሆን ከ 45 ሚሊየን ብር በላይ ለማን እንደተከፈለ የማይታወቅ ገንዘብ ማባከን ተገኝቶበታል፡፡
– በአየር መንገዱ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ሁለት የምድር ዉስጥ እስር ቤት ተገኝተዋል፡፡ በዚህ እስር ቤት ዉስጥ ሰራተኞች ተደፍረዋል፤ ሞተዋል፡፡

Miky Amhara
cc// Amhara Democratic Party /ADP/ CC office
ANRS Communication Affairs Office
Nigussu Tilahun
Addisu Arega Kitessa
Office of the Prime Minister-Ethiopia

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar