0
0
Read Time:41 Second
‼️‼️‼️ሰበር ዜና‼️‼️‼️
⬆️⬆️ምክር ቤቱ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾመwww
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾመ።ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢ ለመምረጥ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብን መርምሮ ያፀደቀው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢነት አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እጩ ባቀረቡበት ወቅትም፥ የሀገሪቱን የምርጫ ሂደት ለማሻሻል የተገባውን ቃል ለማጠናክር እና ለ2012 ዓ.ም ምርጫ ዝግጅት ገለልተኛ የምርጫ ቦርድን ለማጠናከር ያለውን የፓለቲካ ቁርጠኝነት ምስክር ነው ብለዋል። በዚህም ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢነት የቀረቡትን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ አስተያየት ከሰጠ በኋላ የቦርዱ ሰብሳቢ አድርጓል።
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳነትን በራሳቸው ፈቃድ የለቀቁትን ወይዘሮ ሳሚያ ዘካርያን የሚተኩ ይሆናል።
ምንጭ: FBC
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating