0
0
Read Time:47 Second
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉ የገጠር መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረ ግለሰብ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል በአምስት ዓመት ከስድስት ወር እስራትና በገንዘብ #እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጠ።p
ፍርድ ቤቱ ዛሬ ባዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበረው አቶ መልካሙ ታደሰ ላይ ነው።
ግለሰቡ ለመንገድ ሥራ የሚውሉ መሳሪያዎች ግዢ ለመፈፀም በወጣ ጨረታ የግዢ ስርዓቱን ባለመከተል ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብና የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረጉ ውሳኔው እንደተላለፈበት በችሎቱ ተመልከቷል።
የተሰጠውን የመንግስት ኃላፊነት አለአግባብ በመጠቀም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ2008 እስከ 2009 ዓ.ም የተለያዩ መስሪያዎችን ግዢ ለመፈፀም ባወጣው ጨረታ አሸናፊው ድርጅት ላሸነፈበት የውል ማስከበሪያ ሳያቀርብ ውል እንዲገባ በማድረግ የውሉን 30 በመቶ ቅድመክፍያ እንዲፈፀም ትዕዛዝ መስጠቱ ተጠቅሷል።
በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ተቀብሎ በገባው ውል መሰረት መሳሪያዎቹን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሳያቀርብ መቅረቱም በችሎቱ ተመልክቷል፡፡
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በአምስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating