www.maledatimes.com ቴድሮስ ተሾመ ከጠቅላይ ሚንስትሩ በአለ ሲመት ጋር በተያያዘ ተከሰሰ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቴድሮስ ተሾመ ከጠቅላይ ሚንስትሩ በአለ ሲመት ጋር በተያያዘ ተከሰሰ

By   /   November 23, 2018  /   Comments Off on ቴድሮስ ተሾመ ከጠቅላይ ሚንስትሩ በአለ ሲመት ጋር በተያያዘ ተከሰሰ

    Print       Email
0 0
Read Time:48 Second

ቴድሮስ ተሾመ ከጠቅላይ ሚንስትሩ በአለ ሲመት ጋር በተያያዘ ተከሰሰ

የሴባስቶፖል ሲኒማ ባለቤት ቴዎድሮስ ተሾመ ሚያዚያ 27 ቀን በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ በተዘጋጀው የውይይትና የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በአለ ሲመት ልዩ መርሐግብር ኪነጥበባዊ ዝግጅትን እንዲያቀርብ በድርጅቱ ቴድሮስ ፊልም ስራዎች አማካኝነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጋር ሚያዚያ 4 ቀን የገባው የ231 ሺህ ብር ውል በውሉ መሰረት ክፍያ ባለመፈፀሙ ቴአትር ቤቱ ያልተከፈለው የውል ገንዘብ ከነወለዱ እንዲከፈለው ግንቦት 14 ቀን በደብዳቤ የተጠየቀ ቢሆንም ፤ ከተከሳሹ ወገን መልስ ባለመገኘቱ ኅዳር 5 ቀን ክስ አቅርቦበት ነበር። በዚህ ቀን ከተከሳሹ መልስ ያላገኘው ቴአትር ቤቱ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶታል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ አብሮ አደግ ጓደኛ የሆነውና ጠቅላይ ሚንስትሩ ደራአዝ በሚል የብዕር ስም የፃፏቸውን መፅሃፍት አሳታሚና አከፋፋይ የነበረው ቴድሮስ ተሾመ ከፍርድ ቤት የተላከለት ደብዳቤ የደረሰው ሲሆን፤ በዚህም መሰረት በፍትሐ ብሔር አንቀፅ ቁጥር 92 መሰረት ክስ ቀርቦበት ታህሳስ 4 ቀን በፌደራል አንደኛ መደበኛ ችሎት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ታዟል።

አንዳንድ አርቲስቶች ቴድሮስን “የዐቢይ አህመድ ሰራዊት ፍቅሬ ለመሆን ይሞክራል” በማለት ያሙታል።

ለማንኛው ጉዳዩ በህግ ስለተያዘ ውሳኔውን በቅርብ የምንሰማው ይሆናል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar