www.maledatimes.com የራይድ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ሊቆም ነው! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የራይድ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ሊቆም ነው!

By   /   November 24, 2018  /   Comments Off on የራይድ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ሊቆም ነው!

    Print       Email
1 0
Read Time:2 Minute, 36 Second

የራይድ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ሊቆም ነው! azeb worku

share ride

እኔ የራይድ አገልግሎት ተጠቃሚ ነኝ የቴክኖሎጂ ሓሳቡ ለሐገሬ ያበረከተውን አስተዋፅእ በማየት የራይድ አገልግሎት ሠጪዎችን እና የራይድ ፈጣሪዎችን አግኝቼ ምንድነው? ለምንድነው የተከለከላችሁት ? ብዬ ስጠይቅ ያገኘሁት ምላሽ:

ድርጅቱ ያለው ፍቃድ የቴክኖሎጂ ነው ስለዚህ ዘርፍ ቀይሮ በትራንስፖርት ፍቃድ ይሠማራ በሚል ነው አሉኝ ።

ድርጅቱ በዚህ ዘርፍ ለመሠማራት ቢያንስ 30 መኪና ማስገባት አለበት ይላል ህጉ።
ራይድ አሁን እየሰራ ያለው
ሐገር ውስጥ ያሉት እና የንግድ ፍቃድ ያላቸው መኪኖች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ከተጠቃሚዎች ጋር በቴክኖሎጂ የማገናኘት ስራ ነው።
ራይድ ይሄን አገልግሎት በመሥጠቱ
ከከተማችን የመኪኖች ብዛት ጋር የማይመጣጠነው የመንገዶች ስፋት ላይ ሌላ ተጨማሪ መኪና ገብቶ መንገዱ የበለጠ እንዳይጨናነቅ የዓየር ብክለቱም እንዳይጨምር ያለውን መጠቀም እንዲቻል ለትራንስፓርት ችግሩ መፍትሔ የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል ብዬ አስባለሁ።

በዛ ላይ ሐገራችን ባለባት የውጪ ምንዛሪ እጦት ላይ መኪና አስመጡ የሚል ትዕዛዝ አስፈላጊ እና ወቅቱን ያገናዘበ ነው ብዬም አላስብም።

ብድር ይሠጠኝ ሳትል ከቀረጥ ነፃ ይፈቀድልን ሳትል በግል ተነሳሽነት የቴክኖሎጂ ሐሳብ በማፍለቅ ለ 2 ዓመታት ሙከራ አድርጋ የከተማችን የትራንስፖርት እጥረትን ለመፍታት የሞከረችውን ሐሳብ አመንጪ መሸለም እና ማገዝ ባይቻል እንኳን እንዳትሰራ እንቅፋት መሆን ለምን አስፈለገ?

የ ራይድ አገልግሎት ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
የግል መኪናን ወደ ንግድ ቀይረው ፍቃድ አውጥተው የራይድ አገልግሎት ከሚሠጡት መካከል ወደ 150 የሚጠጉት ሴቶች ናቸው። ከእነዚህ ሴቶች መካከል አብዛኞቹ ከዓረብ ሐገር ስደት የተመለሱ ናቸው።

ደሞዛቸው ከኑሮ ውድነት ጋር አልመጣጠን ብሎ ወር አላደርስ ያላቸው በርካታ ሠራተኞችም በትርፍ ሰዓታቸው ራይድ በመሥራት ገቢያቸውን በማሣደግ ኑሯቸውን አሻሽለዋል።

የራይድ ሃሳብ አመንጪዎች አገልግሎቱን ለተጠቃሚዎቹ ለማስተዋወቅ ከ2 ዓመት በላይ ጊዜያቸውን ፣ገንዘባቸውንና እውቀታቸውን ገብረዋል።

በተጨማሪም የራይድን ሓሳብ በሐገራችን ለመተግበር የተነሱት ወጣቶች እውቀት እንጂ ገንዘቡ አልነበራቸውምና ለስራው የሚያስፈልገውን 10,000,000(አሥር ሚሊዮን ብር) የሚያወጡ እና የሥራው ባለቤት የሚሆኑ ባለሐብቶችን ማሳመን እጅግ አድካሚ እንደነበረ ይናገራሉ።
ሐሳባቸው ተሳክቶ ከሁለት ዓመት ብዙ ሙከራዎች ፣ መውደቅ እና መነሳቶች እንዲሁም የማስተዋወቅ ሥራዎች በሁዋላ ሥራው መሥመር ያዘ። ለሌሎችም መንገድ ጠረገ፣ አሠራሩ ጥርት ብሎ ወጣ፣ ትርፍ መጣ . …. የሥራው አዋጭነት ተመሠከረ…

ተከለከለ !

መንገድ ትራንስፖርት ይሄን ያህል ጊዜ ዝም ብሎ ቆይቶ አሁን ሕገወጥ ናቸው ብሎ ማለት እና ለመከልከል መነሳት በየጎዳናው በ3 ቁጥር ታርጋ የራይድ አገልግሎት የሚሠጡ ሠዎችን ማስቆም መኪናቸውን ማሠር ማሥፈራራት ለምን?

በተለይ ሌሎች ነባር የታክሲ አገልግሎት የሚሠጡትን ሠዎች ልክ ጠላት የመጣባቸው በማስመሠል ለጥቃት ማነሳሳት ለምን?
በተለያዩ ቦታዎች የራይድ ሹፌሮች በቡድን ጥቃት ይደርስባቸዋል ፣ መኪናዎቻቸው ላይ ጉዳት ይደርስባቸዋል።

እውን አዲስ አበባ የትራንስፓርት እንጂ የተጠቃሚ እጥረት አለ?
እንኳን የራይድ ትራንስፖርት ስንት ባቡር ፣ አውቶብስ፤፣ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ታክሲ ቢጨመር የትራንስፓርት ፈላጊውን ከሰልፍ እና ከግፍያ አድኖ የትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪዎችን ሥራ ያሣጣል ተብሎ ነው አንዱ በአንዱ ላይ ለጥቃት የሚነሳው?

የራይድን ሁኔታ ያየ ባለሐብት እራሳቸውንና ሐገር ለመጥቀም የእውቀት ሃሳብ ይዘው ከሚነሱ ሠዎች ጋር አብሮ ለማትረፍ ገንዘብ ኢንቨስት ለማድረግ ይነሳሳ ይሆን?

በቴክኖሎጂ እውቀታቸው ሠርተው እራሳቸውንና ሐገራቸውን ለመቀየር የሚያስቡ ወጣቶች ራይድ የብርታት የይቻላል ተምሳሌት ይሆናቸው ይሆን?

እኔ የራይድ ተጠቃሚ ነኝ ስለ ራይድ የምመሠክረው
– የሹፌሩን ሥም ፣ ፎቶ እና አድራሻ የያዘ መረጃ ማወቅ እንደመቻሉ በተለይ ሴቶች በሰዓት ያልተገደበ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያለባቸውን ስጋት የሚቀንስ ፣
ተመጣጣኝ ከክርክር ነፃ የሆነ ቁርጥ ክፍያ ሥርዓት መኖሩ ለተገልጋይ እና ለመንግሥት የግብር ሥርዓት ጠቃሚ እንደሆነ እንዲሁም ከላይ የዘረዘርኳቸው
ለዜጎች የሥራ ዕድል እና የገቢ ማሣደጊያ መንገድ የፈጠረ ለከተማችን የትራንስፖርት እጥረት እና የዓየር ብክለት ችግር ወ.ዘተ. የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ነው።

ስለዚህ ራይድ ትራንስፓርት አቅራቢ ድርጅትን ህገወጥ ብሎ ከመሞገት ህጉን ሰፋ አድርጎ ሁሉንም ማሳተፍ ይበጃል እላለሁ።
#istandwithRIDE

የራይድ አገልግሎት መኖር በግል እና በሐገር ደረጃ ስላለው ጠቀሜታ ወይም ችግር የሚሠማቸሁን በመፃፍ ያገባናል በሉ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar