www.maledatimes.com በመላው አውሮፓ የኢትዮጵያዊያኖች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ህብረት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በመላው አውሮፓ የኢትዮጵያዊያኖች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ህብረት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

By   /   November 24, 2018  /   Comments Off on በመላው አውሮፓ የኢትዮጵያዊያኖች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ህብረት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 36 Second

 

እኛ በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን
በቅርቡ እ.አ.አ በ31ኦክቶበር 2018 ዓ.ም. በፍራንክፈርት የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በውጭ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር የተገናኙበት ስብሰባ ላይ የተፈጸመውን አጠያያቂ ድርጊት በጀርመን እንዲሁም በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያንገላታ ያሳዘነ እና ያስቆጣ ተግባር ነው።

ይህ የለውጥ ሂደት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን እና ንብረታቸውን ያጡበትን አካላቸው የጎደለበትን እና ለስደት የተዳረጉበትን ብዙ ዋጋ ያስከፈለንን የሃያ ሰባት አመታት የግፍ እና የመከራ ዘመን እያስታወስን በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለውጥ በመደገፍ በጀርመን ፍራንክፈርት ለተሰበሰብነው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የኢትዮጵያውያንን በብዙሃነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ባረጋገጠ ተስፋ ሰጪ ቅን እና ሃገራዊ ራእይ በያዘው መልክታቸው እንዲሁም የስብሰባው ተካፋዮች ባሳዩት ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ዝግጅቱ በሰላም ተጠናቋል።
ሆኖም ግን የጠቅላይሚኒስትር አብይን አህመድን የለውጥ ጉዞ ከልብ በመደገፍ ከጀርመን እና ከተለያዩ አውሮፓ ሀገሮች የመጡ ተወካይ ልኡካንን እና የዝግጅቱን ተሳታፊዎችን በማሰናከል እንዲንገላቱ እና ብዙዎቹ እንዲመለሱ በማድረግ በጎን እና ከዉጭ የማይታወቁ ግለሰቦችን ደርቦ በመመልመል አግላይ በሆነ ሃላፊነት እና ግልጽነት በጎደለው ለዝግጅቱ መሳካትበዋናነት ሌት ተቀን ሲደክሙ የነበሩትን አስተባባሪዎች እና እንዲሁም የንዑሳን ኮሚቴ አባላትን መጠቀሚያ በማድረግ ዝግጅቱን አደጋ ላይ በመጣል ለደረሰው መመሰቃቀል እና የዝግጅቱ ተሳታፊዎች መጉላላት እና ስብእና መነካት
አሁንም መተማመን የጎደለው ከፋፋይ አካሄድ ተጠያቂዎቹ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በአውሮፓ ሃገሮች እና በጀርመን የበርሊኑ ኤምባሲ አባሎች እንዲሁም በዋናነት በጀርመን የፍራንክፈርቱ ጀነራል ቆንስላ ጽ/ቤት ነው።
የታዘብነውን የደረሰብንን እንዲሁም በተጨማሪ የተፈጸሙ ስብእናን የነኩ ሁኔታዎች ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው ከመላው አውሮፓ ከመጡ የስብሰባው ተካፋዮች ያቀረቡትን አቤቱታ በመመርኮዝ ጊዜ የወሰደ ማጣራት ካደረግን በሁዋላ በቀላሉ በዝምታ የሚታለፍ ባለመሆኑ ይህን የጋራ መግለጫ በማውጣት በቀጣዩም እኛ በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ አገሮቹ ካሉት የኢትዮጵ ኤምባሲዎች ጋር ጤናማ በሆነ መልኩ በአገራችን ጉዳይ ልንሳተፍበት የምንችለውን አቅጣጫ አስቀምጠናል
ቀጥሎ የተጠቀሱት ከ 1 እስከ 6 ያሉት አንገብጋቢ ነጥቦች እንዲተገበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን
እንጠይቃለን።
1.በጀርመን እንዲሁም በጠቅላላው የአውሮፓ አገሮች ያሉ ያልተደመሩ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አባሎች እንዲለወጡልን።
2.ከጅምሩ አወቃቀሩ አሉታዊ የሆነው እና የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ አባካኝ የሆነው የዲያስፖራ ጉዳዮች ከፍል በጠቅላላው ከኢትዮጵያ ኤምባሲዎች መዋቅር እንዲሰረዝ። አማራጭ እንዲመከርበት።
3.በምንም መልኩ በአውሮፓ ሃገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ነጻ ከሆነው የኢትዮጵያውያን አደረጃጀት ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ነጻነትን የሚነካ ኢዲሞክራሲያዊ ከሆነው የገባር እና አስገባሪ ይዘት ያለውን የጥርነፋ ተግባር እና አዲስ ሙከራ ባስቸኳይ እንዲያቆሙ።የመመሪያ ለውጥ እንዲደረግ።
4.በምንኖርበት አውሮፓ በከፍተኛ ደረጃ የተወገዘውን የድንጋይ ዘመን ዘረኝነት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚከፋፍል በጎጥ እና በቋንቋ ማህበረሰብ ለይቶ ማደራጀት መከፋፈል እና መጥራት
ማንኛውም በአውሮፓ ያለ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባስቸኳይ እንዲያቆም ለወደፊቱም ከዚህ የድሮ ዘመን ድርጊት እና አሰራሩ
እንዲቆጠብ። የመመሪያ ለውጥ እንዲደረግ።
5.የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚያገባቸው ጠቅላላ የሃገራቸው ጉዳይ ላይ የሚመክሩበት አስተዋጾ የሚያደርጉበት እንዲሁም የሚገለገሉበት ብሎም አገራቸውን ያሚያገለግሉበት አገናኝ ድልድይ እንጂ በድርጅት ተጠርንፈው የሚታፈኑበት ውይንም ቅራኔ ውስጥ እርስ በእርስ የሚጋጩበት መደረግ ስለሌለበት ኤምባሲዎቹ ከማንኛውም የፖለቲካ የድርጅት አሰራር ጥርነፋ ነጻ በሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜግነትን መሰረት ያደረገ አገልግሎት እንዲሰጥ ለወደፊቱም በመርህ ደረጃ ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠብ።።የመመሪያ ለውጥ እንዲደረግ።
6.ኤምባሲው ከጎጥ እና ከድርጅት ፖለቲካ ማሰባሰቢያነት ብሎም ጠርናፊነት እና ከፋፋይነት ተግባር ሙሉ በሙሉ እንዲያቆም እንዲታቀብ እና የጸዳ እንዲሆን ባስቸኳይ እንጠይቃለን።
በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ በሚቀጥለው አዲስ የአውሮፓ አመት በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች በሚያደርጉት የስራ ጉብኝት ላይ አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ በየአውሮፓ ሃገራቱ ካሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመገናኘት እንዲመክሩ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
communications@pmo.gov.et
ግልባጭ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
public@mfa.gov.et
ለሁሉ ሚድያዎች
በመላው አውሮፓ የኢትዮጵያዊያኖች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ህብረት
ethiopian.union.europe@gmail.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar