ከህግ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ከተላለፈ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ከሆነ የህወሃት ጽንፈኛ እና ዘራፊ ቡድን ከነበረው የደህንነት አባል እንዲሁም ህዝብን በማፈን እና በመጨቆን ለሃሳባት አመታት በዜጎች ላይ ከፍተኛ በደል አድርሷል ተብሎ ከፍተኛ ክስ የቀረበበት እና በአሁን ሰአት በመቀሌ ከታመ መሽጎ የሚገኛው የቀድሞው የደህንነት ሹም በየትኛውም አቅጣጫ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ የሚል ማዘዣ እንደወጣበት ተገልጿል ። በሌላም በኩል ለአውሮጳ ህብረትም ተመሳሳይ ደብዳቤ መጻፉን የሚጠቁሙ ምንጮች አሉ።
በአለም አቀፍ የወንጀል ክስ ይከሰሳሉ ተብለው ከሚጠበቁት የህወሃት ግንባር ቀደም ወንጀለኞች መካከል የደህንነት ሚንስትሩ አቶ ጌታቸው አሰፋ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው ። አቶ ጌታቸው አሰፋ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ፎⶆቸውን እንኳን በአግባቡ የሚያውቅ ያለነበር ሲሆን የፋና ቴሌቪዥን በስህተት በስብሰባ ላይ በነበሩበት ወቅት ለማሳየት መሞከሩ የሚታወስ ሲሆን እርሳቸውን የሚያውቁ እና በእርሳቸው ስር ከፍተኛ ድብብደባ እና በደል የደረሰባቸው ጋዜጠኞች ማንነታቸውን በፌስቡክ እና በዌብሳይቶቻቸው ሳይቀር ከቴሌቪዥኑ ስርጭት በኋላ ሲያጋሩ መክረማቸው ይታወሳል ፡፤ የእኝህን ወንጀለኛ ጥልቅ መረጃ የአሜሪካ ኤምባሲም የወንጀለኛ ምርመራ ቡድን ጋር በጥምረት ማጥናታቸውን እና ለፍርድ መቅረብ የሚቻልበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚችሉ ምንጮች ይጠቁማሉ። ከሰሞኑ በመቀሌ እና አካባቢዋ በተደረገ ሰልፍ ምክንያት አብዛኛውን የኢትዮጵያን ማህበረሰብ ያስቆጣ ከመሆኑም በላይ ለትግል ተነስተናል ማለታቸው እና ለ፳፯ አመታት ኢትዮጵያ የነጻነትን ጥያቄ ሲያቀርቡ ምንም አይነት ድምጸትን ያላሰሙት እነዚሁ ወገኖች ዛሬ በሌብነት ተጠርጥረው ወደ ዘብጥያ ለወረዱ ባለስልጣናት ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸው …ከኢትዮጵያ ሌብነትን የሚያበረታቱ ዜጎች በሚል ቅጽል ስም እየተሰጣቸው ከፍተኛ ውግዘት በሶሻል ሚዲያ ሲተላለፍባቸው መስተዋላችን ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለህዝብ እና ለሃገር እኩልነት በህግ እና በስርአት የህወሃት አስተዳደር ባወጣው የህግ አዋጅ መሰረት ተገቢውን አሰራር በመጠቀም ማንኛውም ወንጀለኛ ባጠፋው ጥፋት መሰረት ተገቢውን እርምጃ ቢወሰድበት ተቀባይነት ሊኖረው እንደሚችል የትግራይ ሰዎች ቢያገናዝቡት ጥሩ ነበር ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች እንዳሉ አይጠፋም።
ማለዳ መረጃ ማእከል
Average Rating