www.maledatimes.com በሕገወጦች ላይ መንግሥት ጠንካራ አቋም እንዳለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክረተሪ አስታወቁ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በሕገወጦች ላይ መንግሥት ጠንካራ አቋም እንዳለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክረተሪ አስታወቁ

By   /   December 2, 2018  /   Comments Off on በሕገወጦች ላይ መንግሥት ጠንካራ አቋም እንዳለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክረተሪ አስታወቁ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 39 Second
በሕገወጦች ላይ መንግሥት ጠንካራ አቋም እንዳለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክረተሪ አስታወቁ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክረተሪ ቢልለኔ ሥዩም ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ
ብሩክ አብዱ

በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች እንደሚስተዋሉና መንግሥትም የሕግ የበላይነትን ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክረተሪ ወ/ሮ ቢልለኔ ሥዩም ተናገሩ፡፡ ወ/ሮ ቢልለኔ አክለውም በሕገወጦች ላይ መንግሥት ጠንካራ አቋም አለው ብለዋል፡፡

የፕሬስ ሴክሬታሪዋ ይኼንን ያሉት ዓርብ ኅዳር 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በቋሚ ዘጋቢነት ለሚሠሩ ጋዜጠኞች፣ የቋሚ ዘጋቢዎች አመራረጥና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

የሕግ የበላይነትን ለማጠናከር መንግሥት እያከናወነ ካላቸው ሥራዎች በተጨማሪ፣ ተቋማትን ማጠናከር ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል፡፡

‹‹የሕግ የበላይነት ተቋማዊ ገጽታ ይዞ እንዲሄድ በርካታ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው የሚገኙት፡፡ በገለልተኝነት እንዲከናወን የሚደረገው አሠራር ተጠናክሮ ይቀጥላል፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ውጪ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ችግሮች መኖራቸውንና ተረጋግቶ ማየት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፣ ‹‹ከሕግ የበላይነት (በመውጣት) የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ላይ ዕርምጃዎች እየተወሰዱ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ይሁንና ፕሬስ ሴክረተሪዋ በተለያዩ ሥፍራዎች በተለይም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች የደረሱ ጉዳቶች መጠን ምን ያህል እንደሆነ ከመጥቀስ ተቆጥበዋል፡፡

በተያያዘም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርጉት ውይይት በምርጫ ቦርድ መሪነት እንደሚቀጥል የገለጹት ፕሬስ ሴክረተሪዋ፣ ውይይቱ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታን ለማጎልበት ያግዛል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ማክሰኞ ኅዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ያደረጉትን ውይይት በማስታወስ ሒደቱ ዴሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማጎልበት እንደሚያግዝ የጠቆሙት ወ/ሮ ቢልለኔ፣ ውይይቱ የመጀመርያና ዓይነተኛ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

‹‹ውይይቱ የተለያዩ ሚናዎች አሉት፡፡ አሁንም ዴሞክራሲን ማስፋት ላይ ከምናተኩርባቸው ሥራዎች ጋር ተያይዞ በጣም የጎላ ሚና የተጫወተ ስብሰባ ነበር፤›› ብለው፣ ‹‹እስካሁን ያለንን የፖለቲካ ባህል እንዴት ልንቀይረው እንችላለን? ከመቃረን አብሮ ወደ መሥራት፣ እንዲሁም ወደፊት ከለውጡ ጋር ከመጣው ዕርምጃ ጋር አብሮ የሚጓዝ አዲስ የሆነ የፖለቲካ ባህልን ለመፍጠር የጎላ ሚና ይጫወታል ብለን እናምናለን፣ ተጫውቷልም፤›› ብለዋል፡፡

ውይይቱ የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋት ባለፉት ወራት የተደረጉ ዕርምጃዎችን ለማጠናከርና በቅርበት ለመሥራት ያግዛልም ሲሉ አክለዋል፡፡

በቀጣይም ውይይቱ የተለያዩ ፓርቲዎችን እያካተተ እንደሚቀጥል፣ በቀጣዩ ምርጫ አስቀድመው መለወጥ ያለባቸው ጉዳዮች ምንድናቸው የሚለውን የሚያወያይ መድረክ ይሆናል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ለውጦች ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ትኩረትን እየሳቡ እንደመጡ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምንና የኢኮኖሚ ትስስርን ለማምጣት የምታከናውነው ሥራ ላይ ትኩረት እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ለውጡንም ቀጣይነት ያለውና ተቋማዊ ለማድረግ የተቋማት ግንባታ ላይ ትኩረት መደረጉን ፕሬስ ሴክረተሪዋ አክለዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar