www.maledatimes.com ከነትጥቃቸው ቤተ መንግሥት ከገቡ ኮማንዶዎች 66ቱ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ተፈረደባቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከነትጥቃቸው ቤተ መንግሥት ከገቡ ኮማንዶዎች 66ቱ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ተፈረደባቸው

By   /   December 14, 2018  /   Comments Off on ከነትጥቃቸው ቤተ መንግሥት ከገቡ ኮማንዶዎች 66ቱ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ተፈረደባቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:37 Second

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ለማግኘትና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ በሚል ምክንያት ከነትጥቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ገብተው ከነበሩ 216 የመከላከያ ሠራዊት መካከል 66ቱ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ፍርድ እንደተሰጣቸው ተገለጸ፡፡

ሐሙስ ታኅሳስ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. የመከላከያ ሠራዊት ሪፎርምና አገራዊ ሰላምና ፀጥታን በማስመልከት መግለጫ የሰጡ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እንደገለጹት፣ የሠራዊቱ አባላት ሆነው ቤተ መንግሥት ከነትጥቃቸው መግባታቸው በሠራዊቱ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ በመሆኑም፣ አባላቱ እዚሁ ፊታችን ዕርምጃ ይወሰደባቸው በማለት ቁጣቸውን መግለጻቸውን ከፍተኛ መኮንኖቹ ተናግረዋል፡፡ 

Screen grab of PM doing press-ups

በዚህም ምክንያት 66 የሠራዊቱ አባላት በቀዳማዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ፍድር እንደተሰጣቸውና የተቀሩት አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው ተነግሯል፡፡

‹‹ቤተ መንግሥት የሚገባው በምርጫ ነው እንጂ በጠመንጃ አይደለም ሲሉ የሠራዊቱ አባላት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፤›› ሲሉም መኮንኖቹ አስረድተዋል፡፡

በተያያዘም በሠራዊቱ እየተሠራ ያለው የሪፎርም ሥራ ዓመቱን ሙሉ እንደሚቀጥልና በቀጣይም አሁን የተጀመረውን ሪፎርም ጥልቀት የማስያዝ ሥራ እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on December 14, 2018
  • By:
  • Last Modified: December 14, 2018 @ 1:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar