www.maledatimes.com አራዳ የተሰኘው ዜማ ለፍቃዱ ተክለማርያም ላደረገው መልካምነት መገለጫ ነው ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አራዳ የተሰኘው ዜማ ለፍቃዱ ተክለማርያም ላደረገው መልካምነት መገለጫ ነው !

By   /   December 14, 2018  /   Comments Off on አራዳ የተሰኘው ዜማ ለፍቃዱ ተክለማርያም ላደረገው መልካምነት መገለጫ ነው !

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 57 Second

የገንዘቡ ውዝግብ አርቲስቶችን በሙሉ ከልብ አሳዝⶈል ፣ ይህ የእኛነታችን መገለጫችን አይደለም!!

አራዳ የተሰኘው አዲስ ነጠላ የሙዚቃ ዜማ በቅርቡ
መለቀቁ ይታወቃል ግጥም እና ዜማ ደራሲው ድምጻዊው አብዱ ኪያር ሲሆን የዚህን ሙዚቃ የተጫወተው ደግሞ ወጣቱ ድምጻዊ ፍቃዱ ግርማ
ነው ።

አራዳ የተሰኘው ይሄው አዲሱ ዜማ በዩቱብ ላይከተለቀቀ ቀን ጀምሮ ከአርባ አምስት ሺህ አድማጮጭ በላይ ተመልካች ሲኖረው የሙዚቃ ስራው እንዴት ተሰራ እና ምን አይነት ይዞታይኖረዋል ብሎ የገመተ ማንም እንዳልነበረ እና ለምንስ አራዳ ሊሰኝ ቻለ የሚለው አጠያያቂ ጉዳይ ሁላችንንም ትኩረት እንድንስብ አድርጎናል፤ ይሄውም ዋነኛው እና መሰረታዊው ጥያቄ በአርቲስት ፍቃዱ ተክለ ማርያም ለወጣቷ የኩላሊት ታካሚ የእራሱን ጉዳይ አሳልፎ መስጠትነበር ፤ የደራሲውን ቀልብ የሳበው እና በዚያው እለት ምሽቱን ሆዱን ሲያብሰለስለው ቆይቶ ይህንን ዜማ እና ግጥም ሰርቶ ለድምጻዊው ያቀረበለት ።

 በአሁን ሰአት ሰዎች የሰዎችን ንብረት እና ገንዘብ ዘርፈው የግላቸው ማድረግበተጀመረበት ክፉ አለም ውስጥ አንድ ሰው አርቆ በማሰብ  ለወደፊቷሃገር መሪ ልትሆን ለምትችል ወጣት እኔ ህይወቴን ይብቃኝ ታዳጊዋ ህይወቷን ታትርፍ ያለውን ለእርሷ ስጧት ማለቱ ምን ያህል መሰዋእትነትእንደሆነ ላየ እና ለመረመረው ይገባዋል ሲል የአራዳ ግጥም እና ዜማ ደራሲ አብዱ ኪያር ለማለዳ ታይምስ እና ዘሃበሻ  ዘጋቢ ገልጦለታል።  https://youtu.be/FzeyKSjj45E

 በእርግጥም በፍቃዱ ተክለማርያምን ስናጣ ሃገርን እንዳጣን ልንቆጥርበት የምንችልበት
ምክንያት አለን …ያለን አብዱ ኪያር ለምን እንዲህ እንደ አለ ስንጠይቀው ወጣቷ የነገ ሃገር ተረካቢ ነች ሃገር ያለ ተረካቢ ዋጋ
አይኖረውም ፣እርሱ በዘመኑ ብዙ ለፍቷል ዛሬ ላይ በህይወት ባይኖርም በዘመኑ ግን ሃገርን ተረክቦ በተሰጠው የስራ ተሰጥኦ ሃገርን
አገልግሎ ህዝብን አስደስቶ አልፎአል እስከ ዘለአለም የማንረሳው አንጡራ ሃብታችን ነው፤ እርሱ ደግሞ  ያወረሰንም መተሳሰብን እና መፈቃቀርን መከባበርን ሲሆን ዘር ፣ሃይማኖት ጾታ
እና ዜግነትን ሳንለይ እንድፈቃቀር ፣እንድንከባበር ፣አንዱ ለአንዱ ሲቸግረው እንድንረዳው መክሮናል ለገባው ሰው የበፍቃዱ መልእክት
ይህ ነው ሲል ጠቁⶁል ።

በዚህም መሰረት በፍቃዱን ህክምናውን እንረዳለን በሚል መሰረት የተፈጠረው ውዝግብ እና በተነሳው የገንዘብ ማጭበርበር ዙሪያ ሌሎች የኪነጥበብ ሰዎችን ሊያማክል የማይችል እና የአንድንግለሰብ ግለ ጥቅማዊ ብቻ የሚዳሥ መሆኑን ጠቁመው በዚህም መሰረት ሌሎች የኪነጥበብ ሰዎች ስማቸው እንዳይጠፋ እና ከእንደዚህ አይነትክፉ ስነ ምግባር እንዲቆጠቡ ያሳሰቡ ሲሆን ከዚህም ባሻገር ከስማቸው በላይ ለሙያው ክብር ቢሰጡ ማህበረሰባችን ደግ እና እሩህሩህእንደመሆኑ መጠን …አስፈላጊውን ድጋፍ ለመደራረግ ቀላል ነው በማለት አብዱ ኪያር ገልጧል። ለዚህም አራዳ የሚለው ዜማ ለፍቃዱ ለዋለውስራ መታሰቢያነቱን እና የእርሱ የመልካምነት አርአያ የሁላችንም መገኛ መሆን አለበት ብሏል።እንደዚህ ነው ስሚኝ ዘመዴ እንደዚህ ነው ለሰው ይሞታልእንደዚህ ነው ካፈቀረ አንዴእንደዚህ ነው አይገኝም እንጂእንደዚህ ነው እንዲህ በቀላልእንደዚህ ነው ምርጥ ያራዳ ልጅ እንደዚህ ነው ምኑ ይጠላል።=========================== ካራዳ ልጅ ጋራ ጨዋታ መች ይጠገብና ያለው ደስታ ካራዳ ልጅ ጋራ ፍቅር ተይው አይወራ ይቅር ክፋት ምቀኝነት መችያውቅና ወሬና አሉባልታ መችያውቅና ሲጠላም ሲወድም ፊትለፊት ነው ያራዳ ልጅ ማለት እንደዚህ ነውእንደዚህ ነው አራዳ እንዲህ ነውእንደዚህ ነው ነይ ዘመድ አለም እንደዚህ ነው እንዳራዳ ልጅእንደዚህ ነው ቀና ሰው የለምእንደዚህ ነው አይገኝም እንጂእንደዚህ ነው እንዲህ በቀላልእንደዚህ ነው ምርጥ ያራዳ ልጅ እንደዚህ ነው ምኑ ይጠላል። በዚህ ክፉ ዘመን ስስት በበዛበት ሌባ ማፈር ትቶ በሚጀነንበት የሃሰት ነቢያት እጅግ በበዙበት አረመኔው ደፍሮ አማኝ ነኝ ባለበት ሞትን ንቆ ጥሎ ሒይወት ያከበረ እኔ ልሙት ብሎ ሌላ ሠው ያኖረ

አምላኩን ተማምኖ መች ይፈራል ሞት በፍቃዱ አይተናል ያራዳን ሒይወት ለኔ ማለት ትቶ ለኛ እሚል ሲመጣ ራሱን ያሸነፈ ስስትን የረታ ፍቃዱን አብዛልን የላይኛው ጌታ እንደዚህ ነው አራዳ አንዲህ ነው እንደዚህ ነው ነይ ዘመድ አለም እንደዚህ ነው እንዳራዳ ልጅ እንደዚህ ነው ቀና ሰው የለም እንደዚህ ነው አይገኝም እንጂ እንደዚህ ነው እንዲህ በቀላል እንደዚህ ነው ምርጥ ያራዳ ልጅ እንደዚህ ነው ምኑ ይጠላል።ከወንዝ ልጅነት ይርቅ ይዘልናከዘር ከሃይማኖት ከጎሳ ይወጣናሠው ሠው ነው በማለት ማሰብ እሚጀምረውሁሉኑም የሰው ልጅ አንድ አርጎ እሚቆጥረውማንም ይሁን ማንም ብቻ ይሁን ጥሩከየትም ይምጣ ከየት ብቻ ይሁን ጥሩመች ያስፈልግና ብሔርና ዘሩያራዳ ልጅ ይላል ዋናው ነገር ፍቅሩ የሚያመሳስለው አለው ብዙ ነገር ህይወቱን ይሰጣል ላመነበት ነገር አይደራደርም በናቱና ባገርእንደዚህ ነው አራዳ እንዲህ ነውእንደዚህ ነው ነይ ዘመድ አለም እንደዚህ ነው እንዳራዳ ልጅእንደዚህ ነው ቀና ሰው የለምእንደዚህ ነው አይገኝም እንጂ

እንደዚህ ነው እንዲህ በቀላል እንደዚህ ነው ምርጥ ያራዳ ልጅ እንደዚህ ነው ምኑ ይጠላል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on December 14, 2018
  • By:
  • Last Modified: December 14, 2018 @ 2:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar