www.maledatimes.com የህዳሴው ግድብ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ማመንጨት ሥራ ከሁለት ዓመት በኋላ ይጀምራል ተባለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የህዳሴው ግድብ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ማመንጨት ሥራ ከሁለት ዓመት በኋላ ይጀምራል ተባለ

By   /   December 14, 2018  /   Comments Off on የህዳሴው ግድብ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ማመንጨት ሥራ ከሁለት ዓመት በኋላ ይጀምራል ተባለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 1 Second

  1. የግድቡ ሥራ በአራት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሏል

የህዳሴው ግድብ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ማመንጨት ሥራ ከሁለት ዓመት በኋላ ይጀምራል ተባለ

ፖለቲካ

የህዳሴው ግድብ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ማመንጨት ሥራ ከሁለት ዓመት በኋላ ይጀምራል ተባለ

13 December 2018ብርሃኑ ፈቃደ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ ማስተካከያዎች ተደርገውበት ከሁለት ዓመታት በኋላ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ እንደሚጀምር የግድቡ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ገለጹ።

የጥራትና የጊዜ መጓተት ችግሮች በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በኩል በተፈጠሩ ግድፈቶች ሳቢያ ይጠናቀቃል ከተባለውም ጊዜ ዘግይቶ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ 65 በመቶ ላይ ይገኛል። በሜቴክ እንዲገነቡ ውል የተገባባቸው የብረት መዋቅርና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች መጓተትና የጥራት ጉድለቶች የግድቡን ግንባታ ሥራ በተቀመጠለት ጊዜ እንዳይካሄድ አድርጓል ያሉት የግድቡ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ተክሌ ሆሮ (ኢንጂነር) በኤሌክትሮ ሜካኒካልና መሰል ሥራዎች ተስተካክለው በሁለት ዓመታት ውስጥ የመጀመርያው ምዕራፍ ግንባታ እንደሚጠናቀቅም ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል። በጠቅላላው የግድቡ ግንባታ ሥራ በአራት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አስታውቀዋል።

ግድቡ የሚገኝበትን የግንባታ ሒደትና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በተጠራው የውይይት መድረክ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው ምንም እንኳ የግድቡ የሲቪል ሥራዎች 82 በመቶ ቢጠናቀቅም፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎቹ 23 በመቶ ብቻ በመከናወኑ ጠቅላላ ድምር አፈጻጸሙን 65 በመቶ ላይ ገድቦት ቆይቷል።

በመሆኑም ላለፉት ሰባት ዓመታት በግንባታ ላይ የሚገኘውና አራት ዓመታት የተጓተተው የህዳሴው ግድብ ሌላ አራት ዓመታት ይፈልጋል። እስካሁን ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ ቢወጣበትም ለማጠናቀቅ የሚጠይቀው ተጨማሪ ገንዘብ ገና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on December 14, 2018
  • By:
  • Last Modified: December 14, 2018 @ 2:25 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar