www.maledatimes.com የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት ምክንያት ነባር ነዋሪዎች አይፈናቀሉም አለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት ምክንያት ነባር ነዋሪዎች አይፈናቀሉም አለ

By   /   December 23, 2018  /   Comments Off on የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት ምክንያት ነባር ነዋሪዎች አይፈናቀሉም አለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 21 Second

  • ነዋሪዎች በነበሩበት ቦታ የተሻለ ኑሮ እንዲያገኙ የሚያመቻች ጥናት እየተካሄደ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት ምክንያት ነባር ነዋሪዎች አይፈናቀሉም አለ
በመልሶ ማልማት ከፈረሱ አካባቢዎች አንደኛው

ነዋሪዎች በነበሩበት ቦታ የተሻለ ኑሮ እንዲያገኙ የሚያመቻች ጥናት እየተካሄደ ነው

በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከዚህ በኋላ በሚያስተዳድረው ክልል ውስጥ በመልሶ ማልማት ፕሮግራም የሚፈናቀል አንድም ሰው እንደማይኖር አቋም ያዘ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከያዘው አቋም በመነሳት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የመልሶ ማልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ፣ ከመልሶ ማልማት ቦታዎች የሚነሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች በነበሩበት ቦታ እንዳሉ የተሻለ ኑሮ ስለሚያገኙበት ጥናት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የመልሶ ማልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ ለታ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አስተዳደሩ በመልሶ ማልማት የያዛቸው ቦታዎች ላይ የነበሩ ሰዎች በሚካሄደው ልማት እንዴት መካተት እንዳለባቸው ምክረ ሐሳብ ማቅረብ የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡

‹‹ከቦታቸው የሚነሱ ሰዎች የሚቆዩበት ቦታና ግንባታው ከተካሄደ በኋላ እንዴት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እያጠናን ነው፤›› ሲሉ አቶ ተሾመ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የመልሶ ማልማት ፕሮግራም፣ ነባር ነዋሪዎችን ከማኅበራዊ መስተጋብራቸው ነጥሎ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚያሰፍር ነበር፡፡ ነባር ነዋሪዎች ወደ ማስፋፊያ ቦታዎች ሲዛወሩ ደግሞ በቦታቸው ላይ የቆዩ ነባር አርሶ አደሮችም ይፈናቀላሉ፡፡

‹‹ከዚህ ቀደም ነዋሪዎችን በማፈናቀል ሲካሄድ የቆየው መልሶ ማልማት ችግር ያለበት ነበር፤›› ያሉት አቶ ተሾመ፣ ‹‹አሁን የተጀመረው ስያሜው መልሶ መልማት ቢሆንም፣ ከቀድሞ መልሶ ማልማት ጋር ብዙ ልዩነቶች አሉት፤›› ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት በለገሃር፣ በአምስት ኪሎ፣ በጌጃ ሠፈርና በደጃች ውቤ የመልሶ ማልማት ሥራዎችን ለማካሄድ አቅዷል፡፡

እነዚህ ቦታዎች ላይ ያሉ ነዋሪዎች በቦታቸው ተመልሰው ይሰፍራሉ ተብሏል፡፡ ቀደም ሲል በተከለሉ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም ቦታዎች በተለይ በፍርድ ቤት ክርክር፣ በዕግድና በወሰን ማስከበር ምክንያቶች ቦታዎችን ነፃ አድርጎ ወደ ልማት መግባት አልተቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት የሥራ አፈጻጸሙ ደካማ ነበር ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበርካታ ቦታዎች ለመልሶ ማልማት ፕሮግራም ተብሎ በርካታ ቤቶች ቢፈርሱም፣ ግንባታቸው ተካሂዶ አገልግሎት መስጠት የጀመሩት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on December 23, 2018
  • By:
  • Last Modified: December 23, 2018 @ 11:55 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar