www.maledatimes.com በሙስና ወንጀል ተጠርጥራ የታሰረችው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኛ ወ/ሮ ፍፁም የሺጥላ በ50 ሺሕ ብር ዋስ እንድትፈታ ተፈቀደ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሙስና ወንጀል ተጠርጥራ የታሰረችው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኛ ወ/ሮ ፍፁም የሺጥላ በ50 ሺሕ ብር ዋስ እንድትፈታ ተፈቀደ

By   /   December 23, 2018  /   Comments Off on በሙስና ወንጀል ተጠርጥራ የታሰረችው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኛ ወ/ሮ ፍፁም የሺጥላ በ50 ሺሕ ብር ዋስ እንድትፈታ ተፈቀደ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 17 Second

23 December 2018ታምሩ ጽጌ

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የተለያዩ መዝናኛ ዝግጅቶች አስተዋዋቂ የነበረችው ወ/ሮ ፍፁም የሺጥላ፣ ከሜቴክ ጋር በተያያዘ ተጠርጥራ ከታሰረችበት የሙስና ወንጀል በ50 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንድትፈታ ፍርድ ቤት ፈቀደ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ከአንድ ወር በፊት ከሜቴክ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በመመሳጠር፣ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኛ ሳትሆን እንደሆነች በማስመሰልና የድጋፍ ደብዳቤ በማጻፍ ወደ አሜሪካ መሄዷን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱ ይታወሳል፡፡ አሜሪካ ለቆየችባቸው 30 ቀናት 11,500 ዶላር አበል እንደተከፈላትም በመግለጽ መርማሪ ቡድኑ ሲከራከር ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም ፍፁም ኢንተርቴይመንት ለሚባለው ድርጅቷም በስፖንሰር መልክ 954,770 ብር እንደተከፈላት፣ ይኼም የሆነው ከሜቴክ ኃላፊዎች ጋር በነበራት የጥቅም ግንኙነት መሆኑንም መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ ቆይቷል፡፡

መርማሪ ቡድኑ በወ/ሮ ፍፁም ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ታኅሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን፣ በተሰጠው ጊዜ የሠራውን ምርመራ ታኅሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥረኛ ወንጀል ችሎት አስረድቷል፡፡

መርማሪ ቡድኑ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዋ 450 ሺሕ ብር ከሜቴክ መቀበሏን የሚያሳይ አዲስ ሰነድ ማግኘቱን በማስረዳት፣ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብና ኦዲት ለማሠራት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ነበር፡፡

የተጠርጣሪዋ ተከላካይ ጠበቆች ባቀረቡት ተቃውሞ 450 ሺሕ ብር በስፖንሰር አግኝታለች ከተባለው 954,770 ብር ጋር የተካተተ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኦዲትን በሚመለከት ባቀረቡት ተቃውሞ የሜቴክ ኦዲት እስከሚሠራ ድረስ ብዙ ቀናት ስለሚወስድ፣ የእሷ ተለይቶ እንዲሠራና ይኼም ቢሆን እሷ በዋስ ሆኖ መሠራት የሚችል በመሆኑ የዋስትና መብቷ እንዲከበርላት ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ተቀብሎ ሲመለከተው 450 ሺሕ ብር የተባለው ቀደም ብሎ ከተጠቀሰው 954,770 ብር ውስጥ የተካተተ መሆኑን በማረጋጡ፣ የመርማሪ ቡድኑን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ወ/ሮ ፍፁም በ50 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንድትፈታ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ይግባኝ እንደሚል ቢገልጽም፣ አቤቱታውን በጽሑፍ እንዲያቀርብ ተነግሮታል፡፡   

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on December 23, 2018
  • By:
  • Last Modified: December 23, 2018 @ 3:02 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar