0
0
Read Time:33 Second
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ የሪፐብሊኩን የጥበቃ ኃይል አባላት ጎበኙ። የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ማናቸውም ጥቃቶችን ለማስቆምና ለመመከት ያለውን ዝግጁነትና ሙሉ አቅሙን ለማሳየት በዛሬው ዕለት ትርዒት አቅርቧል። የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል አባላት የመንግስት ባለስልጣኖችና ቤተሰቦቻቸውን የጥቃት ዓላማን አንግበው ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከሚሰነዘር ጠለፋና እንግልት ለመከላከልና ለማዳን መዘጋጀታቸውን የሚያሳይ ትርዒት አቅርበዋል፡፡ ኃይሉ የአገሪቱን ሕገ-መንግሥትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በአዲስ የተቋቋመ የደህንነት አካል መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል በከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ያሉትን ኃላፊዎች ከማንኛውም ስጋት እና ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዘዴ መጠቀም ዋነኛ ተግባሩ እንደሆነ ተጠቁሟል። ባለፉት ስድስት ወራት ኃይሉ በሰለጠኑ የደህንነት ባለሙያዎች በመታገዝ ስልጠና እያገኘ እንደነበርና ተግባሩን ለማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን እያደራጀ መቆየቱ ተገልጿል
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating