የፌደራል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነርና የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤ ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ፍፁም አረጋ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።
በማንቼስተር ዩኒቨርሲቲ በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ የማስተርስ ድግሪ ምሩቁ ፍፁም ቀደም ብለውም የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኤጄንሲና የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆንም አገልግለዋል።
አቶ ፍጹም በአዲሱ ሥልጣናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴዎች የመምራትና የማደራጀት ሥራዎችን የመወጣት ኃላፊነት እንደሚይዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሹመቱን በተመለከተ አቶ ፍጹም ለሪፖርተር ሹመቱን አረጋግጠው፣ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ አቶ ፍጹም የተሾሙበትን ኃላፊነት በበላይነት የሚመሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ደሚቱ ሐምቢሳ ናቸው፡፡
አቶ ፍጹም ቀደም ብሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይሠሩ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት ሲመሩ ቆይተዋል፡፡
ሌላዋ ተደራቢ ኃላፊነት የተሰጣቸው ደግሞ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ናቸው፡፡ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ባለፈው ሳምንት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ዋና አስተባባሪነት በተጨማሪ፣ የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የድርጅቱን የዕለት ተዕለት ተግባር የማስፈጸም ኃላፊነት እንደተሰጣቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
አቶ ፍፁም በኢንቨስትመንት ኮሚሽንና በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ላሳዩት የአመራር ብቃት እያመሰገንኩ አሁን በተሾሙበትና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አውራ ሃላፊነት በሚባለው፤ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትጵያውያን በሚኖሩባት አሜሪካ በኢምባሲው ባለስልጣናትና በስደተኛው መካከል ለዘመናት ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት በማደስና በማጠናከር በኩል ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸው ሲሆን ከተጠበቀው በላይ ቀዝቅዞ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
አምባሳደር ፍፁም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ካሳ ተክለ ብርሓንን ይተካሉ።
Average Rating