በተለያዩ የትምህርት ስልጠና እና ከፍተኛ ማእረግ ከሚሰጣቸው እርከኖች መካከል የዶክትሬት ትምህርት ላይ አተኩረው ላጠናቀቁ ማንኛውም የትምህርት አይነት እና ደረጃ ዶክተር ተብሎ መጠራት አግባብነት እንደሌለው ፣ እና ማእረጉ የትምህርት ደረጃ ማእረግ እና እርከን እንጂ ፣በህክምና ላይ ባደረገው ጥናታዊ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ብቻ ዶክተር ተብሎ ሲጠራ ፣ በሃገራችን ኢትዮጵያ ለክብር ዶክትሬት እና ለተለያዩ የትምህርት እርከኖች ላገኙት የዶክትሬት ማእረግ ዶክተር ተብለው መጠራታቸው ፣ የህክምና ባለሙያን የማእረግ የእርከን እንደማራከስ እና በሙያው ላይ ያለውን ትልቅ አሉታዊ ሂደት ክብሩን እንደማሳጣት ነው፡፡
በሃገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ የሚያ እርከኖች ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች ይህንን ክብር ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም የቴትር ባለሙያዎችም ሆኑ ድምሻውያኖች ፣የመድረክ ተዋኛንም ሆነ የፊልም ባለሙያ ወይንም ተያያዥ ስራ ውስጥ ያሉ ሰዎች አርቲስት የሚለውን ልዩ የስራ ስም በማይገባቸው ላይ የሚጠቀሙ ሲሆን አርቲስት የሚባለው ሰው ቅርጽቅርጽ የሚሰራ እና የስነ ጥበብ ወይንም የስእል ባለሙያ እንጂ አዝማሪውም ሆነ ተዋናዩ አለበለዚያም ዳንሰኛው የሚጠቀምበት ሙያ አይደለም ሲሉ ፣ የሰሜን አሜሪካ የዩንቨርሲቲ ምሁር አቶ ተስፋአለም አዲስ ለማለዳ ታይምስ ገልጽዋል፡፡
በሃገራችን ያሉ ምሁራኖች ያለ ስራቸው እና ምግባራቸው በዚህ ማእረግ መጠራታቸው የማይቀፋቸው ወይንም የማይከፋቸው ናቸው ሆኖም ኝ የህክምና ባለሙያው ወይንም ዶክተሩ ክብሩን ሲገፉት ምንም ስሜት የላቸውም ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
በሃገራችን ሊለመድ የሚገባው ነገር ቢኖር ማንኛውም የትምህርት ማእረግ ላይ ዶክትሬት ድግሪ የያዘ ሰው በሙሉ አቶ ተብሎ መጠራት አለበት እንጂ በምንም አይነት መልኩ ዶክተር ተብሎ አይጠራም ይህ ከሆነ ምሁር የተባለውም ሰውም ሆነ ጠሪውም የእውቀት ማነስ አለበት ሲሉ አክለው ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም ዶክተር የሚባለው የህክምና ባለሙያ ብቻ እንደሆነ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
Average Rating