www.maledatimes.com “አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል እንደተሸሸጉ መንግስት መረጃው አለው” – ጠቅላይ አቃቢ ህግ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል እንደተሸሸጉ መንግስት መረጃው አለው” – ጠቅላይ አቃቢ ህግ

By   /   January 2, 2019  /   Comments Off on “አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል እንደተሸሸጉ መንግስት መረጃው አለው” – ጠቅላይ አቃቢ ህግ

    Print       Email
0 0
Read Time:55 Second

የትግራይ ክልል አስተዳደር፣ ከፌዴራሉ ሥልጣን በላይ ሆኗል ማለት ነው?! …. ኤልያስ ገብሩ!
——-

“አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል እንደተሸሸጉ መንግስት መረጃው አለው – ጠቅላይ አቃቢ ህግ

#Ethiopia : የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል ተሸሽገው እንደሚገኙ መንግሥት መረጃ እንዳለው ነገር ግን እሳቸውን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲባል ጥይት በመታኮስ የሌላ ሰው ሕይወት እንዲጠፋ ፍላጎት እንደሌላው FDRE Federal Attorney Generalየፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ) አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ለፓርላማ አሳወቁ።

ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የመሥሪያ ቤታቸውን የአምስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት፣ በዜጎች ላይ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲፈጸም በማድረግ የተጠረጠሩትን አቶ ጌታቸው አሰፋን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል የክልሉ መንግሥት አሳልፎ እንዲሰጥ ጥያቄ ቢቀርብለትም ትብብር ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ከአቶ ጌታቸው ውጪ የክልሉ ተወላጅ ያልሆኑ ተጠርጣሪዎችንም ክልሉ ከለላ እንደሰጠና በሕግ ቁጥጥር ሥር ማዋል አለመቻሉን አስረድተዋል። ፓርላማው በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም ይዞ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ጠይቀዋል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት በጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ማብራራያ አልተደሰቱም። መንግሥትም ሆነ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ ጉዳይ ላይ ፈራ ተባ ሊሉ እንደማይገባ የተናገሩ አንድ የምክር ቤት አባል በደል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን መንግሥት በሕግ እንዲጠየቁ ማድረግ ሳይችል ስለሕግ የበላይነት ማውራት እንደማይችል ገልጸዋል።”

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 2, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 2, 2019 @ 8:51 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar