www.maledatimes.com የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው

By   /   January 4, 2019  /   Comments Off on የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:45 Second

2019-01-03Author: አዲስ ማለዳ

የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር ለማዕድን አሰሳ እና በቅርቡ ለሚጀምረው የኢቲዮ-ጅቡቲ የተፈጥሮ ጋዝ ቱቦ ዝርጋታ ድሮን መጠቀም እንደሚጀምር አስታወቀ።
ሚንስቴሩ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚታየው አስቸጋሪ መልክዓ ምድር የማዕድን አለኝታ ቦታዎችን ለመለየት ስላስቸገረኝ የድሮን ቴክኖሊጂን ልጠቀም ነው ብሏል።
በቅርቡ ለሚጀምረው የተፈጥሮ ጋዝ ቱቦ ዝርጋታም ድሮኖችን ለመጠቀም ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ጋር ተስማቷል።
ከኦጋዴን ተነስቶ ጅቡቲ ድረስ የሚዘልቀው እና ስምንት መቶ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የቱቦ ዝርጋታው ደኅንነቱም እንዲጠበቅ በማሰብ ድሮን መጠቀሙ አስፈልጓል ተብሏል።
ድሮኖቹ በቱቦው ውስጥ የሚተልላለፈውን የጋዝ መጠን የሚለኩ፣ በተፈጥሮ ሊኖር የሚችልን ፍሰት መጠቆም የሚችሉ ሲሆን ከውጭ ደግሞ ቱቦው ጥቃት እንዳይፈፀምበት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ይሠጣሉ። ቱቦው በድሮን እንዲጠበቅ ሦስት ጣቢያዎች ይሰሩለታልም ተብሏል።
እያንዳንዱ ድሮን ከ150 እስከ 300 ኪሎ ሜትር ሲሸፍኑ አንዱ ድሮን እስከ 60 ኪሎ ግራም ክብድት የመሸከም አቅም አለው። ለተከታታይ አምስት ሰዓት አየር ላይ መቆየት እና ስድስት ሺሕ ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችሉ ናቸውም ተብሏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 4, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 4, 2019 @ 3:06 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar