www.maledatimes.com በሃሰተኛ ክስ ልጃቸውን ገድለዋል ተብለው እድሜ ልክ የታሰሩት ታራሚ ህይወታቸው አለፈ በዘለአለም ገብሬ እንደታ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሃሰተኛ ክስ ልጃቸውን ገድለዋል ተብለው እድሜ ልክ የታሰሩት ታራሚ ህይወታቸው አለፈ በዘለአለም ገብሬ እንደታ

By   /   January 5, 2019  /   Comments Off on በሃሰተኛ ክስ ልጃቸውን ገድለዋል ተብለው እድሜ ልክ የታሰሩት ታራሚ ህይወታቸው አለፈ በዘለአለም ገብሬ እንደታ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 19 Second

ለእረጅም ዘመናት የህይወት ጊዜአቸውን በእስር ያደረጉት እና ያለምንም ጥፋታቸው በፍትህአብሔር ክስ የተመሰረተባቸው የሰማኒያ አመቱ አዛውንት ከእረጅም የእስርቤት ስቃይ እና መከራ በኋላ በዛሬው እለት ህይወታቸው ማለፉን ከማረሚያ ቤት የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

እንደ መረጃ ዘገባው ከሆነ አዛውንቱ ምንም በማያውቁት እና በአልተረዱት ሁኔታ ልጃቸው በድንገት ሲያልፍ እርሳቸው ቀጥቅጠው እንደገደሉት አድርገው ፖሊሶች የክስ መዝገብ በማቅረባቸው ምክንያት ወንጀሉ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ወንጀል ምድብ ችሎት እረጅም ዘመን ከታየ በኋላ የእድሜ ልክ እስራት እና የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ፣ ጊዜአቸውን በቃሊቲ እስርቤት ውስጥ በዞን አንድ ማረሚያ ውስጥ ታጉረው ከመኖራቸውም ባሻገር ..ለእረጅም ዘመን የህሊና እስረኛ በመሆናቸው ምክንያት በዞን አድ ውስጥ ባሉት ሁለት ክፍሎች ውስጥ እንደ ትግሳጽ የሚሰጡ ታላቅ አባት እና አስተማሪ የነበሩ ታላቅ ሰው ናቸው ሲሉ በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎች ለማለዳ ታይምስ ገልጸዋል።

ሃጎስ ወልዱ

ሂሩት መለስ

ተከስተ ብርሃን

ሰአዳ ሁሴን እና ብርሃነ መስቀል የተሰኙት ዳኞች በተከሳሾች ላይ የሞት ፍርድ እና እድሜ ልክ እስራት ታራሚዎች በፍርድ ቤት ሳያስቀርቡ ሲፈርዱ የነበሩ ዳኞች እንደነበሩ እና ተከሳሾች ምንም አይነት የወንጀል ክስ ሳያውቁ ብዙ እስረኞች እንደታሰሩ ገልጸዋል ። በሌላም በኩል ፖሊሶች ሙስና በመስራት ወንጀል የሌለባቸውን ወንጀል ሰርታችኋል በማለት እና ገንዘብ ከከፈላችሁ እንለቃችኋለን በማለት ብዙ ንጹሃንን እንደአሳሰሩ ጠቁመዋል። ከእነዚህም መካከል
ተስፋሁን ፈለቀ የተባለ መርማሪ የአምስት መቶ ሺብር በመጠየቅ ምርመራውን አቅላልሁ እያለ ገንዘብ የማይከፍሉትን ንጹሃንን ወደ ማረሚያ የሚወረውር ፖሊስ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በአሁን ሰአት ብዙ ታራሚዎች ያለጥፋታቸው በዞን አንድ ውስጥ ታጉረው እንደሚኖሩ እና አብዛኞቹ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው ግማሾቹ ያለምንም ጥፋታቸው የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው እንደሚኖሩም ገልጸዋል ።

በተለይም አንድ እስረኛ የሞባይል ስልክ ነጥቆ በማምለጡ ምክንያት ተያይዞ ፲፮ አመታትን እስርቤት ከማሳለፉም በላይ እድሜ ልክ የተፈረደበት መሆኑን በጣም አሰቃቂ ነው ሲሉ ምንጮቻችን የጠቆሙ ሲሆን ፣ በሌላም በኩል ደግሞ በቦሌ አካባቢ የባለ ስልጣን ቤት ጠቁመሃል ተብሎ ደህንነቶች መንገድ ላይ አግኝተውት ያሳያቸውን ወጣት እድሜ ልክ እንደ አስፈረዱበት ሪፖርቱ ያስረዳል።

ባለፈው ስምን ወራት ውስጥ ስድስት የገጠር ልጆች የሆኑ ከአስራ ስድስት እስከ ሃያ ሁለት አመታት ያላቸው ወጣቶችን ከማረሚያ ቤት ሊያመልጡ ነው ተብለው በጥይት አጋድመው ደብድበው በፖሊሶች መገደላቸውን ጠቁመዋል ፣ይህ በእንዲህ እንደአለ ደግሞ በማረሚያ ቤት ፖሊሶች እና በመርማሪ ፖሊሶች እንዲሁም በደህንነቶች የሚደርሰው ግፍ የከፋ ከመሆኑም በላይ ሰቆቃው በዝቶባቸው እራሳቸውን የሚያጠፉ ወጣቶች ከፍተኛ ቁጥር እንደአላቸው ጠቁመዋል።

ወርቁ ደምሴ ገብረ ስላሴ የተባለ ታራሚ ደግሞ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ የጭነት መኪና በመስራት ይተዳደር የነበረው ወጣት ፡ሲሆን፡ከጅቡቲ ሲመለስ ባለቤቱ፡ከሌላ፡ወንድ፡ጋር፡ተኝታ በማግኘቱ እና ከወንዱ ጋር ያደረገችውን ግንኙነት ስላናደደው ሲደባደቡ ፣ባለቤቱን ያማገጠው ሰው በቢለዋ ሊወጋው ሲል በሃይል በልጦት በመገኘቱ የተቃራኒውን ወገን እግሩን በቢለዋ በመውጋቱ የተነሳ ከፍተኛ ደም ፈሶት በህይወት ሲያልፍ ይህም ግለሰብ እጁን ለፖሊስ በእራሱ ፈቃድ አሳልፎ በመስጠቱ ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት ፖሊስ በዚህ ሁኔታ እራስህን አሳልፈ ስለሰጠህ ክሱን አንመሰርትም ፣በሌላ ክስ መመስረት አለብን ብለው በድብደባ ጭምር አሳምነውት ክስ እንደተመሰረተበት እና ክሱን የመሰረተበት መርማሪ ያሬድ ታረቀኝ የተሰኘ ፖሊስ ሲሆን በወረዳ አስራ ዘጠኝ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ጋር መሆኑን እና ታናሽ እህቱን በጾታዊ ግንኙነት ካልተገናኛት እድሜ ልክ የሚያስፈርድ ክስ መስርቶ እንደሚያስፈርድበት እንደሚችል ለእህቱ ጭምር ገልጾ ክሱን ይሄው መርማሪ በሚፈልገው መልኩ አድርጎ እድሜ ልክ እንዳስፈረደበት ገልጾአል።

በማረሚያ ቤቶች በተያያዙ ጉዳዮች እና ሌላ ምርምራዊ ሪፖርቶች ማለዳ ታይምስ ተከታታይ መረጃዎችን ይዞ ለመቅረብ ይሞክራል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 5, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 5, 2019 @ 4:55 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar