www.maledatimes.com ፍትህን ያጡ ፍርደኞች ስለ ፍትህ ይጮሃሉ በዘለአለም ገብሬ እንደታ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፍትህን ያጡ ፍርደኞች ስለ ፍትህ ይጮሃሉ በዘለአለም ገብሬ እንደታ

By   /   January 6, 2019  /   Comments Off on ፍትህን ያጡ ፍርደኞች ስለ ፍትህ ይጮሃሉ በዘለአለም ገብሬ እንደታ

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 24 Second

ለአለፉት ፳፯ አመታት በህወሃት መንግስት ብዙ የህግ ጥሰት እንደተደረገ እናስታውሳለን ፣ ብዙዎቻችን ባልሰራነው እና ባላጠፋነው ጥፋት ወንጀለኞች ተብለን ተከሰናል ፣ እንኳን እኛ ልንፈጽመው እና ሰው ሌሎች ቸካኝ ሰዎች ሲፈጽሙት የሚዘገንኑን ወንጀሎች ሲፈጸሙ እንዴት እንደሚያመን ልብ ይሏል።

ለምሳሌ ሃገራችንን የምንወድ ዜጎች ሁሉ ሃገራችንን ለማንም አሳልፈን መስጠት እንደማንችል ከአያት ቅድመ አያቶቻችን ተምረናል ወርሰናል ፣ ሆኖም ግን ወያኔ በምርጫ ፺፯ አመተምህረት ጋዜጠኞችን እና ፖለቲከኞችን የማለዳ ታይምስ አዘጋጅን ቸምሮ በሃገር ክህደት እና በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሶን እንደነበር ይታወሳል ። በወቅቱ ማናችንም ጋዜጠኞች ሆንንን የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የፈጸምነው የዘር ማጥፋት ወንጀል የለም ፣ ወይንም ሃገራችንን ክደን ለሌሎች ሃገር ምስጥራትን አሳልፈን አልሰጠንም ፣ እንደ እነርሱ የሃገራችንን ማእድን አላሸሸንም ፣ሃብት ንብረት በህገወጥ አላፈራንም ወይንም አላሸሸንም ፤ ይህ በሆነበት ነጻ አለም ላይ ወንጀለኞች ተብለን መከሰሳችን ከሚገርመኝ እና ከሚደንቀኝ አንዱ ክስ ነው ።

ይህንን እያስተዋልኩ ዛሬ ላይ ያለ ወንጀላቸው የተከሰሱ ጥቂት ንጹሃን እስረኞችን ሃሳብ ለመዳሰስ እሞክራለሁ ፣ ምናልባትም ሰፋ ባለ ሁኔታ ጥልቅ የሆነ መረጃ ይዜ ለመቅረብ ቃል ስገባ ለዛሬው የእስረኞቹን ሁኔታ ከአዲስ አበባ ፣ ያለው ሪፖርተራችን ቃሊቲ እስርቤት በመሄድ የበአል ውⶀቸውን አስመልቶ የዞን አንድ ታራሚዎችን ለመጎብኘት ሞክሯል የእነዚህን ፍትህ ፈላጊ ወጣቶች ማንነት እና በምን እንደታሰሩ በአጭሩ ጽፎ ልኮልናል ያንብቡት።

አንተነህ አፖሎ  ካሳንችስ ላይ ቤት አሳይተሃል ተብለህ እድሜ የተፈረደበት ሲሆን ፲፭ኛ አመት እስረኛ እንደሆነ ተጠቁሟል። ባሳለፍነው ሳምንታት ውስጥ በሜቄዶኒያ ከሄዱት ውስጥ ታራሚ እስረኞች ፣ እስረኞችን በመወከል ከእስርቤቱ የተሰባሰበ ገንዘብ እና አልባሳትን ለመስጠት ወደ መቄዶኒያ በመጓዝ በአደባባ ይቅርታን ላጠፉትም ሆነ ላላጠፉት በግሃድ እንዲሰጥ ሲማጸን የነበረ ታራሚ ነው

ግሩም ታምሩ የሰው ቤት (ቦሌ አካባቢ የባለስልጣን ቤት) አሳይተሃል ተብሎ ነበር የታሰረው ከዚያም በኋላ በእስር ቤት ሳለ በምርጫ ፺፯ አመተ ምህረት ከቅንጅት ጋር እንቅስቃሴ ታደርጋላችሁ በማለት ፲፰ አመታት እየተሰቃየ ይገኛል። በወያኔ ዘመነ መንግስት ከተፈጸሙት ተደጋጋሚ የሚሰሙ ወንጀሎች ውስጥ የባለስልጣናትን ቤት አሳይታችኋል የሚለው ክስ ሲሆን አንተነህ አፖሎ እና ግሩም ታምሩ በተመሳሳይ ጉዳይ የተከሰሱ ሲሆን ይህ በሃገራችን ባህል ፣ መንገድ ለጠፋው መንገድ ማሳየት ፣ ቤት ለጠፋው ቤት ማሳየት ፣ የተለመደ ሲሆን ሰው እና እንግዳ አክባሪነታችን መገለጫ የሆነው ድንቅ ባህላችን የወንጀል መከሰሻ በመሆን ይሄው የእድሜ ልክ ታራሚዎች ሆነን እየተሰቃየን እንገኛለን ይላሉ ።

ወርቁ
ደምሴ  ወርቁ ደምሴ ገብረ ስላሴ የተባለ ታራሚ ደግሞ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ የጭነት መኪና በመስራት ይተዳደር የነበረው ወጣት ፡ሲሆን፡ከጅቡቲ ሲመለስ ባለቤቱ፡ከሌላ፡ወንድ፡ጋር፡ተኝታ በማግኘቱ እና ከወንዱ ጋር ያደረገችውን ግንኙነት ስላናደደው ሲደባደቡ ፣ባለቤቱን ያማገጠው ሰው በቢለዋ ሊወጋው ሲል በሃይል በልጦት በመገኘቱ የተቃራኒውን ወገን እግሩን በቢለዋ በመውጋቱ የተነሳ ከፍተኛ ደም ፈሶት በህይወት ሲያልፍ ይህም ግለሰብ እጁን ለፖሊስ በእራሱ ፈቃድ አሳልፎ በመስጠቱ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት ፖሊስ በዚህ ሁኔታ እራስህን አሳልፈ ስለሰጠህ ክሱን አንመሰርትም ፣በሌላ ክስ መመስረት አለብን ብለው በድብደባ ጭምር አሳምነውት ክስ እንደተመሰረተበት እና ክሱን የመሰረተበት መርማሪ ያሬድ ታረቀኝ የተሰኘ ፖሊስ ሲሆን በወረዳ አስራ ዘጠኝ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ጋር መሆኑን እና ታናሽ እህቱን በጾታዊ ግንኙነት ካልተገናኛት እድሜ ልክ የሚያስፈርድ ክስ መስርቶ እንደሚያስፈርድበት እንደሚችል ለእህቱ ጭምር ገልጾ ክሱን ይሄው መርማሪ በሚፈልገው መልኩ አድርጎ እድሜ ልክ እንዳስፈረደበት ገልጾአል።

ተካልኝ እርቁ  ባለቤቱን በድንገተኛ ሁኔታ ሞታበት የሞት ፍርድ የተፈረደበት ታራሚ ይቅርታን እና እውነተኛ ፍትህን የሚጠይቅ ታራሚ

በለጠ አሰፋ ከ፭ ሌሎች ጓደኞቹ ጋር ምንም ባልሰሩት ጥፋት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የሚገኙ ሲሆኑ እነዚህ ወጣቶች ደግሞ ከደብረብርሃን አካባቢ ታፍሰው እንደመጡ የፍርድቤቱን

ቢኒያም ጌታቸው ኮብልስቶን ሰራተኛ የነበረ ስሆን በ፲፰ አመቱ ወደ እስር ቤት የመጣ ሲሆን የሞተ ሰው አሳይተውት አንተ ነህ የገደልከው በማለት ከሚጦራት እናቱ እጅ ላይ ነጥቀው እስርቤት ካስገቡት ሰባት አመቱ ሲሆን በአሁን ሰአት በጨለማ እስር ቤት ድብደባ በዝቶበት በፖሊስ ሆስፒታል ውስጥ ለሶስት ቀናት ከተኛ በኋላ እግሩን ኦፕራሲዮን ተደርጎ በአሁን ሰአት በሰዎች እርዳታ የሚንቀሳቀስ እና ፍርደ ገምድል ፍትህ ተፈጽሞበት በስቃይ የሚኖር ወጣት እንደሆነ ተናግረዋል።

ለአለም አበራ ሰው ላንጋኖ በቀለ ሞላ ሆቴል ውስጥ  ወንድሙ  ኢዮስያስ አበራ  በገደለበት ሁኔታ እርሱ እድሜ ልክ ተፈርዶበት እጮኛውን ከሌላ ሰው ጋር ስላገኛት ሁለቱንም ከገደላቸው በኋላ ክሱ በኦሮሚያ ክልል ነጻ በተባልኩበት በሶስት ፍርድ ቤት ነጻ ብሆንም የፌደራል የሰበር ሰሚ ችሎት የእድሜ ልክ ፈርዶብኛ ።  2003 ሰኔ ፳፩ ቀን የፍርድ ውሳኔ የተወሰነብት

ለህገ መንግስት አጣሪ ኮሚቴ በቀረበው መዝገብ ላይ ታይቶ ነጻ ተብዬ ይግባኝ እንዳልጠይቅ የፍርድ ውሳኔ የተወሰነብኝ ሲል ታራሚው ይገልጻል። ሁሉንም ቤተሰብ ታስሮ ነበር የታሰርነው ወንድሜ ጓደኛው፡በበቀለ፡ሞላ፡ሆቴል፡ላይ፡ከአንድ፡የአድዋ፡ሰው፡ጋር፡ግንኙነት ስታደርግ መስማቱን ተከትሎ ሁለቱንም እዚያው በሆቴል ውስጥ ስለገደላቸው እና እኛም ጥቃት ሊፈጽም እንደሄደ በሰማን ጊዜ ከነቤተሰቦቻችን ተሰባስበን እሱን ከእንደዚያ አይነት ወንጀል ለማስቅሞ በነበረበት ሰአት ፖሊስ እናንተም ተባባሪ ናችሁ በማለት ነው ያሰረን ፣ ብዙ ህዝቦች በአሉበት ቦታ ነው እኛ ወንጀሉን እንዳይፈጽም ስንጮህ የነበረው ፣ሆኖም ግን ዞሮ ፍርዱ ወደ እኛ መጣ ፣ በተለይም እናቴ እና እኔ ላይ ከረረብን ግደላቸው እያላችሁ ትጮኹ ነበር ብለው ወንጀልን በማነሣሳት ብለው ከሰሱን ከዚያም ሌሎች ተጨማሪ ብዙ ክሶችን ቸማመሩብን እና ባልፈጸምነው ወንጀል የሞት ፍርደኞች ተባልን ይላል ለአለም አበራ።

የወንድሜ ወንጀል የእኔ አይደለም እኔም ሆንኩ ቤተሰቤ ከዚህ ወንጀል ነጻ ናቸው ፣ ወንድሜ ደግሞ ለፈጸመው ወንጀል አይቀጣ አልልም ሆኖም ግን የእኛ መሰቃየት ተገቢ አይደለም ፣ፍትህ አክባሪዋን አትወድም ይለናል።

ከ2000
አመተ ምህረት ጀምሮ ነጻ ሆኜ ለሶስት አመታት በኦሮሚያ ክልል የተፈረደልኝ  ሲሆን አንድ አመት ታስሬ  ከተለቀኩኝ ከ፫ አመታት በኋላ እንደገና የፌደራል ሰበር ችሎት ፍርድቤቱ እንደገና
አድኖ በመያዝ እድሜ ልክ ፈርዶብኛል እንዲህ አይነት ፍትህ ነው በሃገራችን ላይ እየተተገበረ ያለው ሲል ለአለም አበራ ይናገራል።

የመዝገብ ቁጥር 45595 የተመዘገበ ሲሆን በዚህ መዝገብ ስር ወንድሜ ላጠፋው የእኔ የሞት ፍርድ መቀጣት ምንኛ የሚሉት ፍርድ ነው ይለናል ለአለም አበራ

ይግረም ስንታየሁ ከነቤተሰቦቹ እናቱ አባቱ ፪ ወንድሞቹ  የነፍስ ግድያ የእድሜ ልክ እስራት የታሰሩ ፲፮ አመት ታስረዋል ። የእነዚህ ሙሉ ቤተሰቦች ደግሞ በወቱ በማያውቁት ጉዳይ ሰው ገድላችኋል ተብለው ከነቤተሰቦቹ የታሰሩ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት አባቱን ከእስር የለቀቋቸው እንደሆነ እና ሌሎች ቤተሰቦች በእስር ላይ እንደሚገኙ እና ምንም አይነት ፍትህ ያልተራመደላቸው እንደሆኑ ይገልጻሉ፡ ፍትህ ለእውነት ትቆማለች እንጂ በውሸት የሰውን ነጻነት አትገፍም ሲል የሚናገረው ይገረም እኔ ያለምንም ጥፋቴ ከእነ ቤተሰቤ እስር ቤት ልገባ አልችልም ፣ እኔ ጥፋተኛ ከሆንኩኝ እንኳን ቤተሰቤ ከእኔ እኩል በእስር ቤት መሰቃየት የለባቸውም ፣ላጠፋሁት ጥፋት ቅጣቱን የሚገባኝ እኔ ልሆን ይገባል ሲል ጥያቄውን እንደገና ፍትህን ላጓደሉት ለፍርደ ገምድል ዳኞቹ ጥያቄውን አስተውለው እንዲያውት ይጠይቃል።

አለነ ብላታ ወደ ሱዳን ስትጓዝ ሰው ጭነህ ሰው ሞቶብሃል በመባል በማያውቀው ነገር ፍርደኛ ነው ። ይህ ሰው በወቅቱ ምንም አይነት ሰውም ያላየ የትም ቦታ ያልተንቀሳቀሰ ሲሆን በውሸት ምስክር ተፈርዶበት የህይወት ስቃይን በእስር ቤት እያጣጣማት የሚገኝ ታራሚ እንደሆነ ጠቁሟል።

ዋቅጅራ አበበ  የሞተ እሬሳ አሳይተው ፎቶ ካነሱት በኋላ ወደ እስርቤት አውርደውት ፲፩ አመታት በእስር ላይ ያለ ሲሆን የተፈረደበት የሞት ፍርድ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ሰው ምንም አይነት ቋንቋ አስተካክሎ የማይናገር ሲሆን ከማንኛውም ሰው ጋር የማይግባባ እና ችግሩን እንኳን አስተካክሎ መግለጽ የማይችል ታራሚ ነው ይሉታል ። ጠያቂ ቤተሰብ አጥቶ ለአስራ አንድ አመታት የሚሰቃይ ፍርደኛ ነው ፣ፍትህን ይሻል ይላሉ ።

ልብሴነህ ካሳ የተባለው ታራሚ ከጎንደር አምጥተውት ብልቱን ለሁለት ከከፈሉት በኋላ በስኳር በሽታ ጭምር እየተሰቃየ የሚገኝ ሲሆን ፵፯ አመት ፍርደኛ ሲሆን ከዚህ በላይ ፭ ተጨማሪ ያልታዩ ክሶች ይዞ በማረሚያ ቤት እየተሰቃየ ይገኛል።  ከጎንደር ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቹንም ያላየ ሲሆን በአሁን ሰአት ፮ኛ አመቱን በእስር ቤት እየተሰቃየ መሆኑን እስረኞች ጠቁመዋል።

የተከሰሰበትም ክስ በውል የማይታወቅ ሲሆን ስለ ክሱም ሆነ ስለሚፈጸምበት በደል በፍጹም ምንም ነገር የማያውቅ መሆኑን ይናገራል።

ልብሴነህ ካሳ በአሁን ሰአት በበሽታው ብዛት ቆዳው ልክ እንደ እባብ ቆዳ ከሰዉነቱ ላይ እየተገፈፈ የሚሞትበትን ቀናት የሚጠብቅ ሲሆን በእዚህ እስር ቤት ውስጥ ያለወንጀሌ ከምሰቃይ እትብቴን በቀበርኩባት ጎንደር እቀበር ዘንድ እና የገባሁበትን የማያውቁትን ቤተሰቦችን ሳላይ እንዳልሞት እባካችሁ ፍትህን እሻለሁ ይለናል። ፍትህ ለልብሴነህ ካሳ ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይጠይቃል

 ከሴቶች ታራሚዎች ደግሞ  አንችቱ የማነ የተባለችው ወይዘሪት እጅ እና እግሯ ብረት የተገጠመላት (አካሏ የጎደለ) ፍርደኛ ስትሆን ዘጠኝ አመታትን ታስራለች ፣ውጭ ሰው ልከሻል ተብላ የታሰረች ሲሆን ከዚያም በኋላ ባለስልጣን ጋር ግጭት አለሽ በሚል ክስ ተከሳ አስራ ስምንት አመታት ፍርደኛ እንደሆነች ተገልጿል ። ይህች ፍርደኛ ከፍተኛ የህክምና ችግር ያለባት ከመሆኑም በላይ እንደሴትነቷ ለብዙ ጊዜ በተለያዩ ፖሊሶች ጾታዊ ጥቃት የተፈጸመባት ስትሆን በአሁን ሰአት ላይ የአካሏ መጉደል ሳያንስ የሚፈጸምባት ሰበአዊ መብቶች አለመከበር እና የህክምና ፋሲሊቲ አለመሟላት የህይወቷን ቅጽበታዊ ደስታ የሚነጥቅበት ጊዜ እንደ ደረሰ ታራሚዎች ይናገራሉ ።

ደምሰው ዘሪውሁን የማነ በካሚላት መህዲ ላይ አሲድ ደፍተሃል ተብሎ በውሸት ክስ ተመስርቶበት የእድሜ ልክ እና የሞት ፍርደኛ የሆነ ለአስራ ሁለት አመታት በእስር ላይ ያለ; በዚህ ወጣት ፍርደኛ ላይ የተፈጸመውን በደል ለማሰብ ምንኛ ከባድ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ። አንዳንድ ጊዜ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚባለው ፣ሰው በወንጀሉ ላይ ሳይሳተፍም ሆነ ሳያውቀው በወንጀሉ ተጠርጥሮ እና ተከሶ ፣ያለምንም ምርመራ ወንጀሉን የፈጸምከው አንተ ነህ ተብሎ ፣ በመገናኛ ብዙሃኖች እና በባለሃብቶች እንዲሁም በባለስልጣናት ጫና ንጹህን ሰው ለፍርድ ማቅረብ ምንኛ ያማል ። ፍትህ ለንጹሃን አትጓደል የሚለው የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይህንን ጕዳይ የምታነቡ ሁሉ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ በማጋራት ድምጻቸው ይሰማ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን ቀጣይ የማረሚያቤት ጉዳዮችን እና የአረብ ሃገራት የሴት እህቶቻችንን ግፍ ምን ይመስላል የሚለውን በሰፊው ይዤ ለመቅረብ እኮክራለሁ ።ዘለአለም ገብሬ እንደታ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 6, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 6, 2019 @ 1:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar