www.maledatimes.com በጉለሌና በቦሌ የግዴታ ጋብቻ በብዛት ይፈጸማል ሲሉ የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና ገለጹ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጉለሌና በቦሌ የግዴታ ጋብቻ በብዛት ይፈጸማል ሲሉ የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና ገለጹ

By   /   January 7, 2019  /   Comments Off on በጉለሌና በቦሌ የግዴታ ጋብቻ በብዛት ይፈጸማል ሲሉ የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና ገለጹ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 4 Second

በአዲስ አበባ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ጉለሌና ቦሌ የግዴታ ጋብቻ በብዛት እንደሚፈፀምባቸው ተገለጸ፡፡  ባለፈው ሐሙስ በኢንሽየቲቭ አፍሪካ አዘጋጅነት፣ “ለውጥን በመለወጥ መተግበር” በሚል መሪ ሃሳብ በሞዛይክ ሆቴል ለአንድ ቀን በተካሄደ ስብስባ ላይ 20 የሁለተኛ ደረጃና የልዩ ፍላጐት ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሴት ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ 
የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ክቡር ገና በስብሰባው ላይ እንደገለጹት፤ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ጋር በመተባበር ባካሄደው ጥናት፤40 በመቶ በሚሆኑት ተማሪዎች ላይ ልዩ ልዩ ፆታዊ ጥቃት እንደሚፈጸም አረጋግጠዋል፡፡ ጥቃቱ በሁለቱም ፆታዎች ላይ የሚደርስ ቢሆንም ይበልጥ ተጐጂዎች  ልጃገረድ ተማሪዎች ናቸው ብለዋል፤ጥናቱን በመጥቀስ፡፡   
የስብሰባው ዋና አላማ በትምህርት ቤት አካባቢ በተማሪዎች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ለመቀነስ ምን ማድረግ እንደሚቻል ሃሳብ ለማመንጨት መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ችግሩን ፈጥኖ መከላከል ካልተቻለ የሚያስከትለው ጉዳት ቀላል እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡   
ለተሰብሳቢዎቹ የውይይት መነሻ መረጃዎችን ያቀረቡት፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥርዓተ ፆታ ኃላፊ፣ ወ/ሮ አበባ ዘውዴ፤የግዴታ ጋብቻ በአንዳንድ ክፍለ ከተሞች የሚታይ ቢሆንም በቦሌና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች በብዛት እንደሚፈጸም  አስረድተዋል፡፡ 
በ2010 የመጨረሻዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ 7 ሴት ተማሪዎች በግዳጅ እንዲያገቡ መደረጋቸውን የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ በ35 ሴት ተማሪዎችና በ17 ወንዶች ላይ የፆታ ጥቃት መፈፀሙንና ከጥቃት አድራሾች ውስጥ አባትና አጐት እንደሚገኙበት አስምረውበታል፡፡  
“ለውጥን በመለወጥ መተግበር” በሚል መርህ የሚካሄደው የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ፕሮግራም 20 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለትና አዲስ አበባ በሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ የሚደገፍ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 7, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 7, 2019 @ 4:28 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar