የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሪያድ – ሳዑዲ ዓረቢያ ነብዩ ሲራክ
የኢትዮ-ሳዑዲ የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት የመነሻ ደመወዝ መጠን ወለል 1000 ሣ.ሪ እንዲሆን መግባባት ተደርሷል።
=========
የኢ.ፌዲሪ የሠራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከሳዑዲ አረቢያ አቻቸው አሕመድ ቢን ሱለይማን አል-ራጂ ጋር በሪያድ እ.ኤ.አ በ2017 በሁለቱ አገራት መካከል የተፈረመውን የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት ተግባራዊ በሚሆንበት ዙሪያ ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በጉዳዩም ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
በዚህም ውይይት ወቅት የሠራተኛ መነሻ የደመወዝ ወለል መጠን አንድ ሺህ የሳዑዲ ሪያል እንዲሆንና የሠራተኛውና የአሰሪው መብት በሚጠበቅበት ሁኔታ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በሁለቱ አገራት መካከል የተፈረመው የሠራተኛ ስምምነት ውል በሚተገበርበት ሁኔታና ብሎም የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ከሁለቱ አገራት የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን በየስድስት ወሩ እየተገናኘ አፈጻጸሙን እንደሚገመግም መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም የኢ.ፌዲሪ የሠራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የሳዑዲ አረቢያ ምክትል የሠራተኛና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብዱላህ አቡስነይን መግባባት የተደረሰባቸውን ዐብይ ነጥቦች የያዘ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።
ዝርዝር የሠራተኛ ስምምነት አተገባበር ጉዳይ የሚመለከተውን የሠራተኛ ቅጥር ሞዴል በቀጣይ መግባባት በሚደረሰበት ሁኔታ ላይ ሁለቱ መንግስታት በኤምባሲዎቻቸው በኩል የሰነድ ልውውጥ የሚያደርጉ ይሆናል።
ይህ ከዚህ በታች የምትመለከቱት ጽሁፍ በማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል የተሞላ ነው
የሳኡዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያን ንጹሃን ዜጎች ላይ ያደረሰው ከፍተኛውን ጥፋት አስመልክቶ ብዙ ዜጎችን ያስቆጣ እንደነበር ይታወሳል ፣ ሆኖም ግን የሃገራችን መንግስታቶች ለዜጎቻቸው ያላቸው ክብር አናሳ እንደመሆኑ መጠን እና ብዙውን ጊዜ ከአረብ አገራት ተሰደው በሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ከፍተኛውን የታክስ ጫና እና እንደዚሁም የተለያዩ የቀረጥ ክፍያ ስለሚያስከፍሏቸው የሃገሪቱ መንግስት ከሚገኘው ገቢ ከፍተኛ ተጠቃሚ በመሆኑ የተነሳ በአረብ አገራት የሚሰደዱ ባርነትን የሚፈልጉ ዜጎችን የመላክ ህልውናው በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል ።
ለዚህም ላለፉት ዘመናት ከህወሃት አስተዳደር ጀምሮ እስከ አሁኑ መንግስት ድረስ ይህ ሁኔታ እንዲፈጸም ያለንበት የድህነት አረንቋ በሁለተኛ ደርጃ ግፊቱን ይዟል ፣ በተለያዩ አለማት ብዙ ዜጎቻችን ተሰደው በኤንባሲ በር ላይ የድረሱልን ጥሪ የማይሰሙት አምባሳደሮቻችን ከአረብ አገራት መንግስታት ጋር ዜጎቻቸውን ለባርነት ለመሸጥ ግን ግንባር ቀደሙን ይዘውታል ። እንደምሳሌ ያህል የአለም ደቻሳን አሟሟት የምናስታውስ ይመስለኛል ፣ እንዲህ አይነቱ ክስተት እየተፈጸመ የየትኛውም ሃገር ዜጎቹን ወደ አረብ አገራት ላለመላክ በወሰነበት በዚህ ወቅት በተለይም ፊሊፒንስ ዜጎቻቸውን ወደ ሳኡዲ አረብያ እንዳይሄዱ ማገዳቸውን ተከትሎ እና ዜጋቸውን በሞት ፍርድ ተቀጥታ እንድትገደል በተወሰነበት ወቅት የሃገሩ መንግስት እና ህዝቡ በመተባበር በሰይፍ ከመቀላት አድኗት ወደ ትውልድ መንደሯ ሄዳ ላጠፋችው ጥፋት ቅጣት እንዲፈጸምባት የተደረገ መሆኑን የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የአንድ ሰሞን ወሬ ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአብይም አስተዳደር ይሁን የህወሃት አስተዳደር ይህንን አይነት ድርጊት በማይፈጽሙበት ሁኔታ ሴት እህቶቻችንን ለባርነት መዳረግ ፣ ቀድሞ አሜሪካኖች አስገድደው ከሚወስዱት የባርነት ዘመን በምንም የማይሻል እንደሆነ ግልጽ ነው ። ይሄኛው ባርነት ለየት የሚያደርገው ወደው በእራሳቸው ገንዘብ እና ፈቃደኝነት የሚጓዙት ነጻ ባርነት ነው ።
ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ባርነት በዜጎቻችን ላይ ይብቃ
በግፍ ወደ አረብ አገራት እየላኩ መድረሻቸውን የማንከታተል ከሆነ ማንነታችንን የእርሳን ስለሆነ እኛነታችንን እናስብ ሲል ይገልጣል።
Average Rating