0
0
Read Time:28 Second
በአፋር ብሔራዊ ክልል እንድፎ በተባለ ልዩ ቀበሌ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት አራት ሰዎች መገደላቸውን 13 ሰዎች መቁሰላቸው ታወቀ:: ታህሳስ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ሌሊት በተቀሰቀሰውና እስከ ማክሰኞ ረፋድ በዘለቀው ግጭት ሳቢያ ወደ ትግራይና አዲስ አበባ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች መንገድ ተዘግቶባቸው እንቅስቃሴያቸው ተቋርጦ መቆየቱ ተሰምቷል:: ግጭቱ በቀበሌው ውስጥ ከሳምንት በፊት የሕዝብ የተቃውሞ ሠልፍ ከተካሄደ በኋላ እየተባባሰ እንደመጣ መረዳት ተችሏል:: የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማርገብ የአፋር ክልል ልዩ ኃይል ወደ ቀበሌው መግባቱንና ከታጠቁ ግለሰቦች ጋር ተኩስ መለዋወጡን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል:: በግጭቱ ወቅት የአፋር ብሔራዊ ክልልን ሰንደቅ ዓላማ በማውረድ የሶማሌ ክልልን ሰንደቅ አላማ ለመስቀል የሞከሩ ሰዎች እንደነበሩ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል::
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating