0
0
Read Time:30 Second
አራት የአፍሪቃ መንገዶች በመጪዎቹ 2 ወራት ውስጥ በአፍሪቃ የመጀመሪያ የሆነውን የሲቭል አቭየሽን ጥምረት ለመመስረት ማቀዳቸው ታውቋል፡፡ አራቱ አየር መንገዶች የሞሪሸስ፣ የደቡብ አፍሪቃ፣ የሩዋንዳ እና የኬንያ ሲሆኑ ዓላማቸው አንድ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አየር መንገዶቹ አዳዲስ አሰራሮችን በመከተል በአህጉሪቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ብቸኛ የበላይነት መመከትና ኩባንያዎቻቸውን ማበልፀግ ጭምር መሆኑ ታውቋል፡፡ የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ታህሳስ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ባሰራጩት ዘገባ መሰረት የአየር መንገዶቹ መጣመር የወጪ ቅነሳ እንዲያገኙ ከማስቻል ባሻገር የተሳለጠ የበረራ ማዕከል ለመፍጠር እንዲሁም የኮድ ሼር ስምምነት በማድረግ በርካታ መዳረሻዎችን ለማስፋፋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድንና ከአፍሪቃ ውጭ ያሉትን ኩባንያዎች በመፎካከር በአፍሪቃ ያላቸውን ተደራሽነት ማስፋፋት፣ በጥምረታቸው ለማሳካት ከሚፈልጓቸው መካከል የሚጠቀሱት መሆናቸው ታውቋል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating