0
0
Read Time:43 Second
የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛ ኃላፊዎች በመንግሥት ላይ 319,475,287 ብር ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
በክሱ የተካተቱት የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ የሜቴክ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የግብይትና ሽያጭ ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዲ፣ የአዳማ እርሻ መሣሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የቀድሞ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ፣ የአዳማ እርሻ መሣሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬሽኑ ማርኬቲንግና ሰፕላይ ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት ጉድያ፣ የአዳማ እርሻ መሣሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ጎይቶም ከበደ፣ በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት ቸርነት ዳና፣ እሌኒ ብርሃኑና ረመዳን ሙሳ ናቸው፡፡
ተከሳሾቹ የተጠቀሰውን ገንዘብ በመንግሥት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባለው በሜቴክ ሥር ለሚገኘው የአዳማ እርሻ መሣሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ትራክተሮች ግዥ ወቅት፣ ከኮርፖሬሽኑ የግዥ አፈጻጸም መመርያ ውጭና ያለጨረታ ግዢ እንዲፈጸም በማድረጋቸው መሆኑን ዓቃቤ ሕግ በክሱ በዝርዝር ገልጿል፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating