በናይሮቢ ኬንያ በአንድ መሳሪያ ይዘው በገቡ አሸባሪዎች ጥቃት መፈጸሙን ተገልጿል።
እንደ ሃገሪቱ የመንግስት የደህንነት ጥበቃ፡ሚንስትር፡አገላለጽ መሰረት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ሆቴል ላይ በተፈጸመ በዚሁ ጥቃት ላይ አስራ አንድ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ጠቁመዋል።
በአሁን ሰአት መረጃዎችን በማሰባሰብ እና ማን ይህንን ጥቃት አደረገው ወይንም ፈጸመው የሚለውን ምርምር እያካሄድን ስለሆነ ይህንን ሁኔታዎች አጣርተን ለህዝባችን የምናሳውቅ መሆኑን ይታወቅልን ሲሉ ተናግረዋል የፖሊስ
ኢንስፔክተር ጀነራል ጆሴፍ ቦኔት
አንዳንድ የአይን ተመልካቾች እንደገለጹት ከሆነ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ አይቻለሁ በተለይም በካፍቴሪያው መውጫ በር ላይ ከፍተኛ የሆነ ተኩስ የነበረ ሲሆን የውጭ ዜጎች የሚስተናገዱበት ዋነኛ በር ላይ ነበር ከፍተኛው የተኩስ ልውውጥ የተሰማው ትላለች አንድ በሆቴል ቤት ውስጥ የምትሰራ ወጣት፡ገልጻለች።
በሌላም በኩል ደግሞ የህንጻዎች እና ቤቶች ልማት ሚንስትር ሃላፊ የሆኑት ደግሞ ፍሬድ ማትንጌ በአሁን ሰአት ክስተቱ የተፈጸመበትን እያጸዳን ነው ከዚህም በላይ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር አድርገን ጥፋት ያጠፉትን ለፍትህ እናቀርባለን ሲሉ ተናግረዋል።
በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መጎዳታቸውን ፣መቁሰላቸውን እና ማንነታቸው እንዳልታወቀም ጠቁመዋል ፣ወደ ሆስፒታል የሄዱት ቁጥር የትየለሌ ነው ሲሉም አክለው ገልጸዋል።
የፀረ-ሽብርተኝነት ቡድኖች, ሌሎች የህግ አስከባሪ ድርጅቶች እና አምቡላንስ በናይሮቢ የዌስት ላንድ አከባቢ ውስጥ ወደ ሪቨርሳይድ ድራይቭ ዌስትጌት አከባቢ በሚተላለፈው ቦታ ላይ ደም በደም ሥፍራ ተበትነው ነበር። በአቅራቢያው በናይሮቢ የቼሪሞ ካምፓስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ወደ መንገዱ ተወስደዋል።
አንዳንድ ማህበረሰቦች ደግሞ የጠፉባቸውን ግለሰቦች ፣ወዳጆቻቸውን እና ፍቅረኞቻቸውን ፣ ለማግኘት እክል እንደገጠማቸውም የስልክ ኔትወርክ ችግር እንደገጠማቸውም የማለዳ ታይምስ ሪፖርተር ከናይሮቢ ገልጻለች።
በህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አሁንም በግቢው ውስጥ እየተፈላለጉ እና አብረው የተገናኙት ተጣብቀው ከጓደኞቻቸው ጋር ለመገናኘት የሚሞክሩ ልጥፎችን ምስሎችን ያሳያሉ. አንዳንዶቹ የጽሑፍ መልእክቶቻቸው አልነበሩም ብለዋል. ቀይ መስቀል ቤተሰቦቻቸውን ለማፈላለግ የፍላጎት የስልክ መስመሮችን ለመጥራት የሚፈልጉ ቤተሰቦች ጥያቄ አቅርበዋል።
ፖሊስ በበኩሉ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ የሚለጠፉ ማናቸውንም ፎቶዎች በማየት እንዳይደናገጡ እና በአሁን ሰአት ላይ ፖሊስ በሚያደርገው ምርመራ ትልቁን ትኩረት ሰጥተው መልስ ማግኘት እንዳለባቸው ጠቁⶁል።
ነዋሪዎች በሶሻል ሚዲያ በመስመር ላይ እየተንሰራፋቸው ስለ መረጃ ስለሚያስተላልፉ መረጃን በማረጋገጥ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያልተረጋገጠ ዜና ወይም ምስሎች እንዳይተላለፉ ፖሊስ ጠይቋል። ይህ የማለዳ ታይምስ መረጃ ነው ።
Average Rating