www.maledatimes.com የምዕራብ ጎንደሩን ግጭት የሚያጣራ ቡድን በአስቸኳይ እንደሚላክ ተገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የምዕራብ ጎንደሩን ግጭት የሚያጣራ ቡድን በአስቸኳይ እንደሚላክ ተገለጸ

By   /   January 16, 2019  /   Comments Off on የምዕራብ ጎንደሩን ግጭት የሚያጣራ ቡድን በአስቸኳይ እንደሚላክ ተገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:44 Second

በምዕራብ ጎንደር ኮኪትና ገንዳውኃ አካባቢዎች በአገር መከላከያ ሠራዊትና በአካባቢው ሕዝብ መካከል በተፈጠረው ግጭት የንጹሐን ሕይወት ማለፉን የገለጹት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው በድርጊቱ ማን ምን እንደፈጸመ የሚያጣራ ቡድን በአስቸኳይ እንደሚላክ አስታወቁ፡፡
ቡድኑ ከፌደራሉ መንግሥት የሚወከሉ አባላትን እንደሚያካትት የገለጹት ገዱ ባሳለፍነው ሐሙስ አመሻሽ በሰጡት መግለጫ ‹‹በውይይትና በትዕግስት ችግሩን ለመፍታት ጥረት አለመደረጉ በእጅጉ አሳዝኖናል›› ብለዋል፡፡
ሱር ኮንስትራክሽን የተባለ ድርጅት በአካባቢው ለሚሰራቸው የመንገድ ግንባታ ሥራዎች ተሽከርካሪዎቹን ከአንዱ ፕሮጀክት ወደ ሌላው ሲያዘዋውር በመከላከያ ሠራዊት ማሳጀቡንና ይህም ከአካባቢው ፀጥታ አንጻር ተገቢ መሆኑን የገለጹት ገዱ፣ የተፈጠረው ግጭትና የሰው ሕይወት መጥፋት ግን በምንም ዓይነት መለኪያ ተገቢ ሊሆን እንደማይችል አስረድተዋል፡፡
ትናንት መግለጫ የሰጡት የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ‹‹መከላከያ እራሱን ተከላከለ እንጅ ሰው አልገደለም›› ያሉ ሲሆን ‹‹አድፍጦ የታጠቀ ኃይል ወደ ሠራዊቱ መተኮሱን ተከትሎ ሠራዊቱ ራሱን ለመካለከል የወሰደው እርምጃ ስህተት ከነበረበት መከላከያ ሠራዊት እንደ አገር ይቅርታ ከመጠየቅ አልፎ ለተጎጅ ቤተሰቦችም ካሳ ይከፍልላል›› ስለማለታቸው የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ዘግበዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 16, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 16, 2019 @ 4:34 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar