www.maledatimes.com የአማራ ክልል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም 221 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልገው ገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአማራ ክልል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም 221 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልገው ገለጸ

By   /   January 16, 2019  /   Comments Off on የአማራ ክልል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም 221 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልገው ገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:33 Second

የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኤጀንሲ እና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ቢሮ በክልሉ የሚገኙ ተፋናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም 221 ሚሊየን ብር (8 ሚሊየን ዶላር) እንደሚያስፈልገው ገለጸ።
በክልሉ የሚገኙ ተፈናቃዮች እንዴት መረዳት እንዳለባቸው አቅጣጫና ዕቅድ ያስቀመጠው ቢሮው፤ ለተጎጂዎች የምግብ፣ የጤና እና የትምህርት አገልግሎት ለማቅረብ አፋጣኝ ዕርዳታ ያስፈልገኛል ብሏል።
ተጎጂዎቹ በጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኽምራ ዞኖች የሚገኙ ሲሆን በአገሪቷ በነበረው አለመረጋጋት የተነሣ ከአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች አንዲሁም ከጅቡቲ ከባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ጀምሮ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ናቸው።
የዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው እስከ ባለፈው ኅዳር 2011 ድረስ 14 ሺህ የሚሆኑ ተፋናቃዮች በአማራ ክልል ይገኛሉ። በተጨማሪ 320 ተፈናቃዮች ከተለያዩ ቦታዎች በየሳምንቱ ወደ ክልሉ እንደሚገቡ የድርጅቱ መረጃ ያሳያል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 16, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 16, 2019 @ 4:40 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar