0
0
Read Time:42 Second
የስድስተኛው ዓመት ጉዞ ዓድዋ ተጓዦች የዐይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል ገቡ፡፡ የኢትዮጵያ ዐይን ባንክ፣ ሰዎች በሕይወት ካላፉ በኋላ የዐይን ብሌናቸውን እንዲለግሱ በማድረግ በሕይወት ያሉ ሰዎች ብርሃናቸው እንዲመለስላቸው በሚል የተመሰረተ ነው፡፡
ከመስራቾቹም በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እሳቸውም በሕይወት እያሉ በገቡት ቃል መሠረት ከኅልፈታቸው በኋላ የዐይን ብሌናቸውን ለግሰዋል፡፡
የዘንድሮው የጉዞ ዓድዋ ተሳታፊዎችም ይህንኑ በጎ ምግባር ለመፈጸም ቃል በመግባት ጉዟቸውን ጀምረዋል፡፡ የዘንድሮው ጉዞ በዓድዋ ጦርነት የምስራቁን የኢትዮጵያ ጦር በመምራት ከሐረር ለተነሱት ራስ መኮንን መታሰቢያነት በሚል ቀደም ብሎ ከሐረር የተጀመረ ሲሆን ከሐረር የተነሱት እግረኞች አዲስ አበባ ከጠበቋቸው ተጓዦች ጋር ተቀላቅለው ጉዟቸውን ቀጥለዋል፡፡
በተያያዘ ጉዞው ከወትሮው በተለየ በደብረ ብርሃን መሆኑ ቀርቶ በእንጦጦ፣ ሙከጡሪ፣ ለሚ፣ መርሐቤቴ፣ ሚዳ፣ ጃማ ደጎሎ አድርጎ በወረ ኢሉ ደሴ የሚያልፍ ይሆናል። ይህ መስመር በአብዛኛው የጠጠር መንገድ መሆኑ ለተጓዦቹ ፈታኝ ሊሆን ይችላል ቢባልም የዓድዋው ጦርነት ጉዞ የተደረገበትን መስመር ለመከተል ይህ መንገድ መመረጡ ታውቋል።አጠቃላይ ጉዞው 1010 ኪሎ ሜትር ይረዝማል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating