0
0
Read Time:30 Second
የአዲስ አበባ የውሃ ችግር የከተማዋን ነዋሪ ለብዙ እንግልት የዳረገ እንደሆነ ይታወቃል:: በመሆኑም መንግሥት ባወጣው መግለጫ በከተማ ያለው የውሃ ሥርጭት በፈረቃ የሚዳረስና ፍላጎቱና አቅርቦቱ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ መ/ቤቱ በሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚጠናቀቁ 3 የውሃ ፕሮጀክቶች ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል::
ይህንንም እውን ለማድረግ በአያት አካባቢ የሚለማና በቀን 68 ሺ ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም ያለው ፕሮጀክት በሚቀጥለው ዓመት ተጠናቆ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል::
የለገዳዲ የከርሰ ምድር ውሃና የገርዲ ግድብ ፕሮጀክቶች በቀን 159ሺ ኪዩብ የማምረት አቅም ያላቸው ሲሆን እነዚህም በ2014 ይጠናቀቃሉ ተብሏል:: አሁን በአዲስ አበባ ያለው የውሃ ፍላጎት በቀን 930ሺህ ሜትር ኪዩብ ቢሆንም የመዲናዋ የውሃ የማምረት አቅም ግን 574 ሺህ ሜትር ኪዩብ ነው::
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating