www.maledatimes.com በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ በሶማሊያ ጥቃት መፈጸሙን የመካላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ በሶማሊያ ጥቃት መፈጸሙን የመካላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

By   /   January 19, 2019  /   Comments Off on በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ በሶማሊያ ጥቃት መፈጸሙን የመካላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:47 Second

በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ በሶማሊያ ጥቃት መፈጸሙን የመካላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተግባር ላይ የነበሩ ወታደሮች ኮንቮይ ላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸማቸውን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ለጋዜጠኞች በላከው መግለጫ መሰረት እንዳመለከተው፣ ‹‹በሠራዊቱ ላይ ጥቃት የደረሰው ኮንቮዩ ከቡራሃካባ ወደ ባይዶአ በመጓዝ ላይ እያለ ሲሆን፣ ሠራዊታችን ጥቃቱን በጽናት በመመከት ኮንቮዩን ባይዶአ ይዞ ገብቷል፤›› ብሏል፡፡

ሠራዊቱ ካሁን ቀደም በርካታ የአልሸባብ ጥቃቶችን በመመከት አልሸባብን ያዳከመው መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፣ በአሁኑ ጥቃትም አልሸባብ በቀቢፀ ተስፋ የሠራዊቱን ንቅናቄ ለመግታት ሙከራ እንዳደረገ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ሠራዊቱ የአልሸባብን ጥቃት ተከትሎ ጠንካራ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ በስምሪት ላይ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ዓርብ ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሠራዊት አራት መኪኖች ላይ ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ የሠራዊቱ አባላት ተገድለዋል የሚል ዘገባ የወጣ ቢሆንም፣ የመከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ጥቃቱ ምን ያክል ጥፋት እንዳደረሰ አልገለጸም፡፡

ሆኖም የመከላከያ ሠራዊት በአሚሶም ተልዕኮ በሶማሊያ ሰላም በማስፈን ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስታውሷል፡፡ በሌላም በኩል የአልሸባብ ሰራዊት የኢትዮጵያን ወታደር ከገደለ በኋላ በጭነት ማመላለሻ አውቶሞቢል እየጎተተ የሚያሳይ ምስል መልቀቁን ለመረዳትም ተችሏል።

ማለዳ መረጃ ማእከል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 19, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 19, 2019 @ 11:55 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar