www.maledatimes.com በመንግሥት የታቀደው ፕራይቬታዜሽንና የኢኮኖሚ ሪፎርም የሚመራበት ፍኖተ ካርታ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ጀመረ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በመንግሥት የታቀደው ፕራይቬታዜሽንና የኢኮኖሚ ሪፎርም የሚመራበት ፍኖተ ካርታ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ጀመረ

By   /   January 20, 2019  /   Comments Off on በመንግሥት የታቀደው ፕራይቬታዜሽንና የኢኮኖሚ ሪፎርም የሚመራበት ፍኖተ ካርታ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ጀመረ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 39 Second

በመንግሥት የተያዙ ግዙፍ ኩባንያዎችን በሙሉና በከፊል ወደ ግል ይዞታ እንዲዘዋወሩ (ፕራይቬታይዝ) ለማድረግና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርም ለማከናወን የተያዘው ዕቅድ የሚመራበት ፍኖተ ካርታ፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታወቀ።

አንድ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ፍኖተ ካርታው ፀድቆ ወደ ሥራ ከተገባ ከሁለት ወራት በላይ አስቆጥሯል።

ፍኖተ ካርታው መንግሥት በእጁ የሚገኙ ግዙፍ ኩባንያዎች በሽያጭ ወደ ግል ይዞታ የሚተላለፉበትን መሠረታዊ ማዕቀፎችና ሒደቶች የነደፈ ሲሆን፣ መንግሥት ካቀደው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር ተጣጥሞ መፈጸም እንዳለበት የታሰበ መሆኑንም ኃላፊው አስረድተዋል።

የፀደቀው መሪ ዕቅድ (ፍኖተ ካርታ) በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ኮሚቴ የበላይነት እንዲፈጸም መወሰኑንና ለዚህ አማካሪ ኮሚቴ ተጠሪ የሆነ ዓብይ ኮሚቴ በገንዘብ ሚኒስትሩ እንደሚመራ ያስቀምጣል።

የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተለየ ሁኔታ ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል በመሸጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በተመለከተ፣ በዘርፉ የካበተ ልምድ ያለው የትራንዛክሽን አማካሪ እንዲሰይሙ የሚፈቅድ መሆኑም ታውቋል። የመንግሥት ኩባንያዎች በሽያጭ ከመዘዋወራቸው አስቀድሞ አስፈላጊ የሆኑ የሕግ ማሻሻያዎች ተረቀው በፓርላማ ወይም በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቅ እንደሚኖርባቸው ስምምነት ላይ ሲደረስ፣ ይኼንንም በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስትሩ የሚመራው ዓብይ ኮሚቴ እንዲያከናውነው ተወስኗል፡፡ ይህ ሥራም ከታቀደው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር የሚጣጣምና የግል ባለሀብቶችን ሚና የሚያጎለብት፣ እንዲሁም ጤናማ ተወዳዳሪነትን የሚያጠናክር መሆን እንደሚገባው መወሰኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

የትግበራ እንቅስቃሴው ከተጀመረ በኋላ መውጣት ይገባቸዋል ተብለው የተለዩ የሕግ ማዕቀፎች መኖራቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ የቴሌኮም አገልግሎት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ሕግና የኢንቨስትመንት አዋጅን ማሻሻልና የመንግሥት ኢንተርፕራይዞች አዋጅ ይገኝበታል ብለዋል።

የቴሌኮም ኤጀንሲው ሥልጣን የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የንግድ ፈቃድ መስጠትና መቆጣጠር ሲሆን፣ በመንግሥት ዕቅድ መሠረት ከሦስት ዓመት በኋላ ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎት ለሚሰጡ የግል ኩባንያዎች ፈቃድ መስጠት ሊጀመር እንደሚችል ጠቁመዋል።

የኢንቨስትመንት ሕጉን በማሻሻል ለውጭ ኩባንያዎች ዝግ የተደረጉ ዘርፎችን ክፍት በማድረግና ውድድር በማስፈን፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን ለማፋጠን  መታቀዱን ገልጸዋል።

በሎጂስቲክስና በትራንስፖርት ዘርፎች የውጭ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያውያን ጋር በሽርክና እንዲገቡ ለማድረግ መታቀዱንም ኃላፊው አስረድተዋል።

በአጠቃላይ በመንግሥት የተያዙ ግዙፍ ኩባንያዎችን በጥንቃቄና ግልጽነት በተሞላበት ሒደት ወደ ግል በማዘዋወር፣ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የተመዘገበውን ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ ተሻለ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር የዕቅዱ መሠረታዊ ዓላማ መሆኑን ጠቁመዋል። የመንግሥት ኩባንያዎች ወደ ግል ይዞታ በሙሉ በሚዘዋወሩበት ወቅት ከሠራተኞች ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ጉዳዮችም በቅድሚያ እንዲጤኑና መፍትሔ ከወዲሁ እንደሚበጅ ኃላፊው አክለዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 20, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 20, 2019 @ 1:06 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar