www.maledatimes.com በተቀናጀ መንገድ የሚመሩ ፀረ ለውጥ አስተሳሰቦች ለአገራዊ ለውጡ ተግዳሮት እንደሆኑ ኢሕአዴግ አስታወቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በተቀናጀ መንገድ የሚመሩ ፀረ ለውጥ አስተሳሰቦች ለአገራዊ ለውጡ ተግዳሮት እንደሆኑ ኢሕአዴግ አስታወቀ

By   /   January 20, 2019  /   Comments Off on በተቀናጀ መንገድ የሚመሩ ፀረ ለውጥ አስተሳሰቦች ለአገራዊ ለውጡ ተግዳሮት እንደሆኑ ኢሕአዴግ አስታወቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 37 Second

አሁን በአገሪቱ እየተከናወነ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ ምንም እንኳን ጥልቅ፣ ሰፊና ትልቅ ተስፋን ይዞ የመጣ ቢሆንም በተቃራኒው ሥጋቶች እንዳሉበት ‹‹ሕዝባዊ መሠረት የሌላቸው ፀረ ለውጥ አስተሳሰቦች በተቀናጀ መንገድ እየተመሩ ተግዳሮት ሆነውበታል፤›› ሲል፣ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መገምገሙን የግንባሩ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የግንባሩ ሊቀመንበር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከተመረጡ ወዲህ ሁለተኛ ስብሰባውን ያደረገው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ ከጥር 7 ቀን እስከ ዓርብ ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በአገራዊ ለውጥና ያሉበት ተግዳሮቶች ላይ በሊቀመንበሩ ለስብሰባው የተዘጋጀ ጽሑፍ መሠረት በማድረግ ተወያይቷል፡፡

‹‹ከለውጡ በተቃራኒ ያሉ ኃይሎች ሕዝቡን ለማደናገርና ድጋፍ ለማግኘት እንዲያመቸው ለውጡን ተከትሎ በሕዝቡ ውስጥ ያሉ ብዥታዎችንና በለውጡ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአመራር ግድፈቶችን፣ እንዲሁም ማንነትንና ሌሎች አጀንዳዎችን ምክንያት በማድረግ ጽንፈኛ አካሄድ በመከተል የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈጸም ሲሉ በዜጎች ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስና ዜጎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ እየሠሩ እንዳሉ ታይቷል፡፡ የለውጡ አደናቃፊ ኃይሎች በሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር በመታገዝ ግጭትና መፈናቀል እንዲፈጠር፣ ኮንትሮባንድና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመሳሰሉ የኢኮኖሚ አሻጥሮች በመሳተፍ ለውጡን ለመግታት እየተረባረቡ እንደሚገኙ ገምግሟል፤›› ሲል የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ግንባሩ በራሱ ውስጥ በለውጡ ምንነት፣ በለውጡ ውስጥ በሚኖር ሚናና የወደፊት አቅጣጫ ላይ አንድነት ኖሮት እየተጓዘ በመሆኑ በአባል ፓርቲዎች መካከል የአካሄድ ግድፈቶች መኖራቸውና የእርስ በርስ መጠራጠሮች የውይይቱ አጀንዳ ነበሩ፡፡

ሆኖም የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ ካሁን በፊት ሲደጋገሙ የነበሩ ሐሳቦች ላይ ያተኮረና አዲስ ነገር ይዞ መምጣት የተሳነው እንደሆነ የሚተቹ አሉ፡፡ ይኼንን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የስብሰባው ተካፋይ የነበሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ይኼኛውን ስብሰባ ለየት የሚያደርገው አገሪቱ አሳሳቢ ሥጋት እንደተደቀነባትና ልትበታተን ትችላለች የሚል አስተሳሰብ ተይዞና ታምኖበት የተደረገ መሆኑን በመግለጽ፣ በሊቀመንበሩ የተዘጋጀው ጽሑፍም ይኼንኑ እንደሚያስረዳ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሁሉንም ነገር በውጫዊ አካል እያሳሰብን አገር ልንበትን ነው›› መባሉንም አክለዋል፡፡

ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ኢሕአዴግን እንደ ፓርቲ ማጠናከር የውይይቱ አጀንዳ እንደነበርም አውስቶ፣ ‹‹ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ ሌብነትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፈጽሞ እንዳይደገሙ በቂ ክትትል ማድረግና ለዚህ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ዝንባሌዎችን በሁሉም የሥራ መስክ እየፈተሹ መጓዝ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፤›› ብሏል፡፡

በአገሪቱ ከአሁን ቀደም የተፈጠሩ ችግሮችን በሕወሓት ማላከክን በጋራ ለመመከት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለሪፖርተር የገለጹት የስብሰባው ተሳታፊም፣ ‹‹ከአሁን በፊት ላጠፋነው ጥፋትም ልማትም በጋራ ኃላፊነት ለመውሰድ ተግባብተን ወጥተናልም፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 20, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 20, 2019 @ 1:12 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar