www.maledatimes.com ጠ/ሚ/ር ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ቀዳማይ እመቤት ሮማን ተስፋዬ ቤተ-መንግስት ገቡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጠ/ሚ/ር ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ቀዳማይ እመቤት ሮማን ተስፋዬ ቤተ-መንግስት ገቡ

By   /   November 1, 2012  /   Comments Off on ጠ/ሚ/ር ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ቀዳማይ እመቤት ሮማን ተስፋዬ ቤተ-መንግስት ገቡ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 27 Second
አቶ መለስ ዜናዊን በመተካት ከአምስት ሣምንታት በፊት ቃለ መሃላ የፈፀሙት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ባለፈው እሁድ ከነ ቤተሰቦቻቸው ወደ ቤተ-መንግስት ገብተዋል።

እንደ ቪ.ኦ.ኤ ዘገባ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያምና ቀዳማዊ እመቤት ሮማን ተስፋዬ ወደ ቤተ-መንግስት ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ይሁንና አቶ ሀይለማርያም እስካሁን አቶ መለስ ዜናዊ ይጠቀሙበት የነበረውን ቢሮ መጠቀም አልጀመሩም።

ምንጮች እንዳሉት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥራቸውን እያካሄዱ ያሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀላቸው ጊዜአዊ ቢሮ ሆነው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ላለፉት አምስት ሣምንታት ብስራተ-ገብርኤል ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወደ አራት ኪሎ እየተመላለሱ ለመሥራት መገደዳቸው፤የብዙዎችን ትኩረት ስቦ መቆየቱ ይታወሳል።

ለዚህም ምክንያቱ የቀድሞዋ ቀዳሚት እመቤት አዜብ መስፍን ቤተመንግሥቱን ለቅቀው ለመውጣት ፈቃደኛ አለመሆን እንደነበረ፤ በተደጋጋሚ መዘገባችን አይዘነጋም።

አንድ የኢትዮጵያ መሪ ከቤተመንግሥት ውጭ ሲኖር፤ አቶ ኃይለማሪያም የመጀመሪያው ናቸው።

ዘግይቶም ቢሆን ወይዘሮ አዜብ ቤተ-መንግስቱን በመልቀቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝና ቀዳማዊ እመቤት ሮማን ተስፋዬ ከሦስት ሴቶች ልጆቻቸው ጋር በ አቀባበል ታጅበው እሁድ ዕለት ቤተ-መንግስት ገብተዋል።

ከአስር ቀናት በፊት ቤተ-መንግስቱን የለቀቁት ወይዘሮ አዜብ መስፍንም ወደተዘጋጀላቸው መኖሪያ ቤት መግባታቸው ተገልጿል።

አንድ የኢትዮጵያ መሪ ከቤተመንግሥት ውጭ ሲኖር፤ አቶ ኃይለማሪያም የመጀመሪያው ናቸው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 1, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 1, 2012 @ 9:54 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar