www.maledatimes.com የአሜሪካ እርዳታ በግማሽ ቢሊዮን ዶላር ሊቀነስ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአሜሪካ እርዳታ በግማሽ ቢሊዮን ዶላር ሊቀነስ ነው

By   /   January 26, 2019  /   Comments Off on የአሜሪካ እርዳታ በግማሽ ቢሊዮን ዶላር ሊቀነስ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 42 Second

2019-01-25Author: ሳምሶን ብርሃኔ

አሜሪካ ለሚቀጥሉት 11 ወራት ለኢትዮጵያ የተለያዩ የልማት ፕሮግራሞችን ለማስፈፀም እንዲሁም ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ የምትሰጠውን ዕርዳታ በግማሽ ቢሊየን ዶላር (13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር) በላይ ልትቀነስ እንደምትችል ታወቀ። ይህ የአገሪቷን በጀት አምስት በመቶ የሚሸፍን ሲሆን በአሁኑ ወቅት ካለው አለመረጋጋት ጋር ተዳምሮ አገሪቷን ችግር ላይ እንዳይከታት ተሰግቷል።
በቅርቡ ይፋ የሆነው የአሜሪካ ኮንግሬሽናል የውጭ ሥራዎች በጀት መሠረት፤ በኢትዮጵያ ሁሉንም ያማከለ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለማጠናከር እንዲሁም ጤና እና ትምህርት ላይ የሚተገበሩ ፕሮግራሞችን ለማስፈፀም ወደ 226 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር በጀት ለማጸደቅ በአሜሪካ መንግሥት ቀርቧል።
አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት የምትሰጠውን ዕርዳታ በ13 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የሚቆርጠው በጀቱ፤ በኢትዮጵያ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ላይ ችግር አያመጣም ቢባልም ከባለፈው ዓመት ሐሳብ ከቀረበው ጋር ሲነፃፀር በ8 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር (234 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር) ያነሰ ነው። ወደ 2.8 ሚሊየን ዜጎች ባለፈው ዓመት የተፈናቀሉባት ኢትዮጵያ፥ ከአሜሪካ ዕርዳታ በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚ ነች።
በ2017 ኢትዮጵያ ወደ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ከአሜሪካ ያገኘች ሲሆን እስከ ባለፈው ዓመት አጋማሽ ድረስ ወደ 347 ሚሊየን ዶላር ወስዳ ነበር። ቁጥሩ እየቀነሰ ቢመጣም፤ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው በኢትዮጵያ አሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኛ እንደገለፁት፤ ከዚህ ቀደም ከፍተኛው ገንዘብ ለሰብኣዊ ዕርዳታዎች ስለሚመደብና በዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደዚህ ዓይነት ችግር ይከሰታል ተብሎ ስለማይገመት በጀቱ አሁን ሊያነስ ይችላል። ‹‹ስለዚህም አሁን ላይ የተመደበው በጅት ትክክለኛውን የሚደረገውን ድጋፍ ላያሳይ ይችላል›› ብለዋል።
ይሁን እንጂ፤ አሜሪካ ቅነሳ ያደረገቸው ሰብኣዊ ዕርዳታ ላይ ብቻ አይደለም። ለአብነትም አሜሪካ ግጭትን አፈታትና ማስወገድ ላይ የምታደርገው ድጋፍ በዘጠኝ እጥፍ ቀንሶ 20 ሺሕ ዶላር ደርሷል። በተመሳሳይ፤ መልካም አስተዳደርን ለማጎልበት ኢትዮጵያ የመደበችው በጀት ከሁለት ሚሊየን ዶላር ወደ 60 ሺሕ ዶላር ዝቅ ብሏል።
ለጤና እና ተያያዥ ጉዳዮች አሜሪካ ታደርገው የነበረው ድጋፍም ከ179 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወደ 169 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ዝቅ እንዲል ተደርጓል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም አገሪቷ ትመድብ የነበረው ዕርዳታ ከ 28ነጥብ 4 ሚሊየን ዶለር ወደ ሁለት ሚሊየን ዶላር ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
በሌላ በኩል፤ ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎችን ለመርዳት አሜሪካ ወደ 76 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ተመድቦ የነበረ ቢሆንም፤ ለ2019 ግን የተመደበ ምንም ገንዘብ የለም። ግብርና ላይ ለሚተገበሩ የልማት ፕሮግራሞች ደግሞ ወደ 50 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር የተያዘ ሲሆን የዛሬ ዓመት ከነበረው በአምስት ሚሊየን ዶላር ያነሰ ነው።
ከዚህ ባሻገር፤ የግሉ ዘርፍ ተፎካካሪነት ለማሳደግ ወደ ግማሽ ቢሊየን ዶላር አሜሪካ በባለፈው በጀት ዓመት መድባ የነበረ ቢሆንም፤ ይህ በ2019 ከነበረው 200 ሚሊየን ዶላር እንዲቀነስ ተደርጓል። በተመሳሳይ፤ ለአካባቢ ጥበቃ የተመደበው ወደ 46 ሚሊየን ዶላር በያዝነው የፈንጆች ዓመት እንደማይኖር ተገልጿል። በዓመት ለሰብኣዊ እርዳታ በዓመት ወደ 243 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ይመደብ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን እንዲቀር ተድርጓል።
ይሁን እንጂ፤ በጂኦተርማል፣ በፀሐይ፣ በነፋስ፣ በውሃ እና በተመሳሳይ የኃይል አቅርት ፕሮጀክቶች ላይ የግሉ ዘርፍን ኢንቨስትመንት የሚያሳድጉ አዳዲስ ሕጎች እና ደንቦችን ለማዘጋጀት እንዲሁም የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ውጤታማ ለማድረግ እና ለማሰራጨት አሜሪካ የአንድ ሚልዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደማተደርግ በወጣው የአሜሪካ ኮንግሬሽናል የውጭ ሥራዎች በጀት ላይ ተገልጿል። ኤች አይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኙ ሰዎች መድሃኒት ለማቅረብ እና ተያያዥ ሥራዎችን ለመተግበር 69 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ዕርዳታ ለኢትዮጵያ እንደሚቀርብም በበጀቱ ላይ ተገልጿል።
በተጨማሪ ኢትዮጵያ በሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ለምታደርገው የሰላም ማስከበረር ስራዎች 60ሺሕ ዶላር ዕርዳታ አሜሪካ መድባለች። ገንዘቡም ወታደራዊ ሞያዊነትን ለማሳደግ እና በአገሪቷ ሰላም አንዲሰፍን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው መንግሥት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተደጋጋሚ የውጭ አገራትን ለመርዳት የሚወጣው በጀት ለማስቀነስ ሐሳብ ማቅረቡን የአሜረካ ሕግ አውጪዎቸ መቃወማቸው ይታወሳል። እስካሁን ያልጸደቀው በጀቱ ይሉኝታ ያገኘ፤ እንደ አሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ያሉ ተቋማት የሚመደበው ገንዘብ በ33 በመቶ ቀንሶ 16 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ይሆናል።
ይህ በተለይም 70 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በግጭትና በድርቅ ምክንያት በተፈናቀሉበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 26, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 26, 2019 @ 11:00 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar