www.maledatimes.com ሸዋሮቢት ለአደዋ ተጓዦች ደማቅ አቀባበል አደረገች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሸዋሮቢት ለአደዋ ተጓዦች ደማቅ አቀባበል አደረገች

By   /   January 26, 2019  /   Comments Off on ሸዋሮቢት ለአደዋ ተጓዦች ደማቅ አቀባበል አደረገች

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 52 Second

“በምቾች የሚያንገላቱት ሸዋሮቢቶች”

ጉዞ_ዓድዋ_6

~ለራስ አሉላ ክብር ለ4 ደቂቃ ያልተቋረጠ እልልታና ሆታ ተደርጓል።

123ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ለማክበር ዘንድሮ ለ6ኛ ግዜ የሚካሔደው የእግር ጉዞ 48 አባላትን በማሳተፍ 12ኛ ቀኑን እንዲህ ባለው ሁኔታ አሳልፏል

*የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች፤ የቀውት ወረዳ ኃላፊዎችና የከተማው አስተዳደር ደማቅ አቀባበል አድርገው ለተጓዦች በድምሩ የ11,000 (አስራ አንድ ሺህ) ብር የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል።

*የከተማው ወጣቶች ጋሽ አበጋዝ በተባሉ አባት አስተባባሪነት ለተጓዦች አስደናቂ የቁርስ ግብዣ ያደረጉ ሲሆን እንደ አባትነታቸውም ተጓዦችን መርቀው “ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ይህ መንፈስ ነው” በማለት ሁሉም የጀመረውን ጉዞ በድል እንዲጨርስ ተመኝተዋል።

*የከተማው ከንቲባ አቶ አካሉ ወንድሙ በደማቁ የአቀባበል ስነሥርዓት ላይ ተገኝተው ለተጓዦች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን “የዓድዋ ድል መላው ኢትዮጵያዊያንን ባለ ታሪክ ያደረገ አብይ ታሪካችን በመሆኑ በቀጣዪ አመት ከተማችንን የሚወክሉ ተጓዦች እንደምናዘጋጅ ቃል እንገባለን” ሲሉ ተናግረዋል።

*ሸዋነሽ ይመር የተባሉ የሸዋ ሮቢት ነዋሪ ተጓዦችን በጥሩ መስተንግዶ ከተቀበሉ በኋላ የአባታቸው ቅድመ አያት ስመጥሩው የዳግማዊ ምኒልክ ፈረስ አባ ዳኘው ባልደራስ አዛዥ ዲቡ መሆናቸው በማስታወስ የዚህ ታሪካዊ ጉዞ አባላትን የዓድዋ ድል በዓል እንዲደምቅ ለሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

*የሸዋ ሮቢት ነዋሪዎች ከከተማው መግቢያ እስከ መውጫ ድረስ በሆታና በእልልታ ተጓዦችን በማጀብ ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት ገልፀዋል።

*በአቶ ሉሌ ሞላ እና በአቶ ሙሐመድ (ኬንያ) አስተባባሪነት በርካታ የሸዋሮቢት ከተማ ወጣቶች ከቁርስ ግብዣው መዋጮ የተረፋቸውን ገንዘብ ለተጓዦች ስንቅ ይሆን ዘንድ ያበረከቱ ሲሆን ተጓዦች የተደረገላቸውን ደማቅ አቀባበል በማድነቅ “በምቾት የሚያንገላቱ ሸዋሮቢቴዎች” የሚል ቅጽል ስም ሰጥተዋቸዋል።

*የከተማው ነዋሪዎች በተሰበሰቡበት ደማቅ ዝግጅት ላይ በዛሬው እለት 132ኛ አመቱን የያዘውን ታላቁን የዶጋሊ ድል በማሰብ ለጀግናውን የአፍሪካ ቀዳሚ ጄኔራል ራስ አሉላ አባነጋ 4 ደቂቃ የወሰደ የክብር እልልታ ሆታና ጭብጨባ በማድረግ ባለውለታ የሆኑትን ጀግና አክብረዋል።

*ከተማው የፀጥታ አካላት የትራንስፖር አገልግሎት ሰራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ላደረጉት የላቀ ተግባር የጉዞ ዓድዋ አዘጋጆች ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።

*በተያያዘ መረጃም ልክ እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም በተመሳሳይ ሁኔታ ከአንጎለላ ተጓዦችን የተቀላቀለችው አዲሷ ውሻ፤ በደብረሲና ቁልቁለት መንገድ ላይ በደረሰባት ድንገተኛ የመኪና አደጋ የኋላ ሁለት እግሮቿ መራመድ ስለተሳናቸው ተጓዦች እየተቀባበሉ በመሸከም ጉዞውን ቀጥለዋል። የተጎዳን ሰው ቶሎ እንዲሽር “የውሻ ቁስል ያድርግልህ” እንደሚባለው ሁሉ፤ በዓድዋ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ አገልግሎት የሰጡ እንስሶችን የምታስታውሰው ይቺ ውሻ ቶሎ ትሽር ዘንድ ተጓዦች ከልባቸው ተመኝተዋል።

*በባዶ እግሩ የሚጓዘው ኤርሚያስ መኮንን ዛሬም ጉዞውን እንደቀጠለ ነው። የአዲስ አበባና የአካባቢው ነዋሪዎች የእሱን ጥሪ ሰምተው ለተቸገሩ ሰዎች የጫማ እርዳታ ማድረግ በመጀመራቸው ከፍ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።

*ከተማቸው ሰላም እያለች ትተዋት ወደ ዓድዋ በእግር የዘመቱት የድሬ ተጓዦች ከመላው የጉዞ ዓድዋ 6 አባላት ጋር በመሆን ለድሬዳዋ ሰላም ተመኝተዋል።

ፍቅር_ለኢትዮጵያ!!

ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም!!

Via- Yared Shumete – ያሬድ ሹመቴ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on January 26, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 26, 2019 @ 1:16 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar