0
0
Read Time:39 Second
ረቡዕ፣ ጥር 15 የሱማሌ ክልል መንግሥት ካቢኔ ባደረገው ስብሰባ ስድስት የክልሉን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ወስኗል።
ከኃላፊነት ከተነሱት ውስጥ የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ ይገኙበታል።
የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊውም ምክትላቸው በነበሩት አብዱላሂ መሐመድ ተተክተዋል።
‹‹ለአመራሮቹ ከስልጣን መነሳት ምክንያት የሆነው በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ዑመር መሐመድ እና በአህመድ ሽዴ ሊቀ መንበርነት በሚመራው የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሕሶዴፓ) አመራሮች መካከል ኹለት ቡድን መመስረቱ ነው፤ በቡድኑ መካከልም የሥልጣን ሽኩቻ ተፈጥሯል›› የሚሉ መረጃዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወሩ ነው።
ይሁንና ‹‹የክልሉን ገዢ ፓርቲ ኢሶሕዴፓንና የክልሉን መንግሥት አስመልክቶ በማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ›› ነው ሲሉ አዲሱ ቃል አቀባይ አብዱላሂ መሐመድ ለኢዜአ በሰጡት ምላሽ አጣጥለዋል።
ኢሶሕዴፓ በነሐሴ 2010 በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ባደረገው ግምገማ፣ ሦስት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና አምስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማንሳቱ ይታወሳል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating