www.maledatimes.com የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ7,700 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የግብር ዕዳ ምሕረት ማድረጉን አስታወቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ7,700 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የግብር ዕዳ ምሕረት ማድረጉን አስታወቀ

By   /   February 1, 2019  /   Comments Off on የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ7,700 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የግብር ዕዳ ምሕረት ማድረጉን አስታወቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:55 Second

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ7,700 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የግብር ዕዳ ምሕረት ማድረጉን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከከተማው ምክትል ከንቲባ አቶ እንዳወቅ አብቴና ከገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ ጋር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ የተጣለባቸው ግብር ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ እንዲታይላቸው ሲጠይቁ ለቆዩ 6,000 ነጋዴዎች፣ እንዲሁም በግብር ይግባኝ ተከራክረው ለተፈረደባቸው 1,780 ነጋዴዎችም ምሕረት እንዲደረግላቸው ካቢኔያቸው መወሰኑን አስታወቁ።

ምክትል ከንቲባው ይህን ያስታወቁት የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለሥልጣን በጠራው ከተማ አቀፍ የታክስ ንቅናቄ መድረክ ላይ ነው። በቅርቡ በገቢዎች ሚኒስቴር ‹‹ግዴታዬን  እወጣለሁ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ›› በሚል መርሐ ግብር የተጀመረው አገር አቀፍ ንቅናቄ አካል የሆነውን የከተማውን ንቅናቄ ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባው፣ አስተዳደራቸው መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጡ የታክስ ሪፎርሞች መጀመሩን ገልጸዋል።

የታክስ ሪፎርም ዕርምጃዎቹ ማንኛውም የከተማ ግብር ከፋይ በፍላጎቱ ላይ የተመሠረተና መክፈል የሚችለውን ብቻ እንዲከፍል እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባው ይፋ አድርገዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከተማው የሚገባውን ግብር እንዲሰበስብ፣ ነጋዴውም ሆነ የትኛውም ግብር ከፋይ ፍትሐዊ ግብር የሚጠየቅበት አሠራር ተዘርግቷል ያሉት አቶ ታከለ፣ ያልተገባ ግብር ተጠይቆም እንደሆነ ለመንግሥትም ለነጋዴም ሳይወግን በፍትሕ ያለ አድልኦ መፍትሔ የሚሰጥ የግብር ይግባኝ ኮሚሽን መቋቋሙን አስረድተዋል፡፡ የከተማው ገቢዎች ባለሥልጣን በዚህ ዓመት ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዷል። ከዚህ ውስጥ ከታክስ የሚሰበሰብው 34.5 ቢሊዮን ብር ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on February 1, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 1, 2019 @ 2:16 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar