www.maledatimes.com የአዲሱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆቴል የቻይና ኩባንያ ያስተዳድረዋል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአዲሱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆቴል የቻይና ኩባንያ ያስተዳድረዋል

By   /   February 2, 2019  /   Comments Off on የአዲሱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆቴል የቻይና ኩባንያ ያስተዳድረዋል

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 39 Second

በ65 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ ሰካይ ላይት ሆቴል ዕዳውን ከፍሎ እስኪጨርስ በቻይናው ኩባንያ ‹‹ግራንድ ስካይ ላይት ሆቴል ማኔጅመንት›› አስተዳደር ሥር እንደሚሆን ተገለፀ። በቻይና ብሔራዊ የአየር ቴክኖሎጂ ዓለም ዐቀፍ የምህንድስና ኮርፖሬሽን የተገነባው ይህ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል የግንባታ ዕዳውን በጨረሰ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥር እንደሚሆን ታውቋል። ለሆቴሉ ግንባታ የወጣው ወጪ 35 በመቶ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሸፈነ ሲሆን ቀሪው 65 በመቶ ደግሞ ከቻይናው ኤክዚም ባንክ በተገኘ የብድር ድጋፍ እንደሆነ ታውቋል።

አስተዳዳሪ ኩባንያው ከ30 ዓመታት በፊት በ298 ሚሊዮን ዩዋን የተቋቋመ ሲሆን ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሆቴሎችን በዋናነት ዓላማ አድርጎ እየሠራ ይገኛል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በአሁኑ ሰዓት በቻይና፣ በሞንጎሊያ እና በሌሎች የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት 60 ሆቴሎችን እያስገነባ እና እያስተዳደረ የሚገኝ ኩባንያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ኩባንያው በዘርፉ ከእስያ አገራት በመውጣት ወደ ቀረው የዓለም ክፍል አድማሱን እያሰፋ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በዚህም ረገድ በአሜሪካ፣ በቬንዙዌላ እና በኢራን የሆቴል ዘርፍ ላይ ለመሠማራት ያቀደ ሲሆን በአፍሪካ ውስጥ በኢትዮጵያ በቀዳሚነት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ በኬኒያ እና ታንዛኒያ ሆቴሎችን ለማስገንባትና ለማስተዳደር ዕቅድ እንዳለው ታውቋል።

ለኩባንያው በአፍሪካ የመጀመሪያ ሥራው የሆነው የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ከውጭ አገር ተቋሪጮች በተጨማሪ አገር በቀሉ የአማካሪ ድርጅት ̋ስለሺ ኮንሰልት˝ የማማከር ሥራው ተሠርቷል።

የኢትዮጵያን በጎብኝዎች ተመራጭ መዳረሻነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ከተለመደው የሆቴል አገልግሎት በተለየ ደንበኞችን ለማርካት ታስቦ የተገነባ መሆኑን አየር መንገዱ ለአዲስ ማለዳ የገለፀ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየጊዜው ለሚያወጣቸው ጥቅል የጉዞ እና የጉብኝት መርሃ ግብሮች ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጨምሮ ገልጿል። ሆቴሉ 373 የተለያ ደረጃ ያላቸው ክፍሎች፣ አንድ የመዋኛ ገንዳ፣ አራት ዓለም ዐቀፍ ምግቦች የሚስተናገዱበት የመመገቢያ አዳራሽ እና እስከ 2ሽሕ ሰው የመያዝ አቅም ያለው የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ለሚኖራት ̋የኮንፍረንስ ቱሪዝም˝ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

በ40ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ የተንጣለለው ይህ ሆቴል በቅርቡ በሚጀምረው የሆቴሉ የምዕራፍ ሁለት ግንባታ ሲጠናቀቅ ያሉትን የክፍሎች ብዛት ወደ 1 ሺሕ ከፍ እንደሚል በዕቅድ ተይዟል። ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን ሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው ሆቴሉ በአሁኑ ሰዓት ለስምንት መቶ ሰዎች በቋሚነትና በጊዜያዊነት የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ለማወቅ ተችሏል።

በፈረንጆች 2016 ግንባታው የተጀመረው የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተያዘለት የጊዜ ገደብ የተጠናቀቀ ሲሆን ነገ ጥር 19 በይፋ ተመርቆ ሥራ ይጀምራል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on February 2, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 2, 2019 @ 11:26 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar