www.maledatimes.com “የተያዝኩበትን ምክንያት አላወኩም“ ያሉት የደህንነት አባል ይግባኝ እንዲጠይቁ ተፈቀደላቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“የተያዝኩበትን ምክንያት አላወኩም“ ያሉት የደህንነት አባል ይግባኝ እንዲጠይቁ ተፈቀደላቸው

By   /   February 2, 2019  /   Comments Off on “የተያዝኩበትን ምክንያት አላወኩም“ ያሉት የደህንነት አባል ይግባኝ እንዲጠይቁ ተፈቀደላቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 48 Second

ከሰብኣዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ በነጎህ አጽብሃ መዝገብ ጉዳየችው እየታየ ከሚገኙ 33 ሰዎች መካከል 14ኛ ተጠርጣሪ የሆኑት ግለሰብ የፌድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዬን በሚገባ እየተመለከተልኝ አይደለም በሚል ቅሬታቸውን አሰሙ። ሰይፈ በላይ የተባሉት ተጠርጣሪ ቅሬታቸውን ያሰሙት ረቡዕ፣ ጥር 16 በመዝገቡ ከአንድ እስከ ዐሥራ ስድስት የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በታየበት ዕለት ነው።

ተጠርጣሪው “በእኔ ላይ የቀረበ አንዳችም ምስክር በሌለበት ሁኔታ ላለፉት 77 ቀናት በእስር ላይ ነው የምገኘው፥ ይህን ተመልክቶም ፍርደ ቤቱ ምላሽ እየሰጠኝ አይደለም” ብለዋል። ተጠርጣሪው እንደገለጹት መርማሪ ፖሊስም በምን ጉዳይ በቁጥጥር ሥር እንደዋለኝ በቂ የሆነ ማብራሪያ አልተሰጠኝም በማለት ይህ ባልሆነበት ሁኔታም በተደጋጋሚ ጉዳዩን ለችሎቱም ባሰማም ምንም ምላሽ አላገኘሁም የሚል ቅሬታቸውን ለችሎቱ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪው በማይመለከተኝ ጉዳይ ላይ ምስክሮች አሉ እየተባለኩና በሌሎች መዝገቦችም ከሕግ ውጭ በሆነ መንገድ ምርመራ እየተካሄደብኝ ነው የሚል መከራከሪያቸውን ለችሎቱ አሰምተዋል። በተጎጂዎች ላይ የደረሰ የሕክምና ማስረጃ እያፈላለኩ ነው በሚል በተደጋጋሚ በመርማሪ ፖሊስ የሚቀርቡ ማስረጃዎችም መሠረተ ቢስ ናቸው ብለዋል። በተለያዩ ጊዜያት የመርማሪ ፖሊስ አባላት መለዋወጥ ያለውን መረጃ እየለዋወጠው ነው የሚል መከራከሪያ ነጥብም አሰምተዋል። “እኔ በዋስ ብወጣ የማጠፋው ነገር የለም” ያሉት ተጠርጣሪው በማላውቀው ጉዳይ መጉላላት እየደረሰብኝ ነው ሲሉም ቅሬታቸውን በምሬት ገልጸዋል።
ችሎቱ በበኩሉ ተጠርጣሪው እያገኙ ባለው ፍትሕ ላይ የሚያቀረቡት ቅሬታና ይግባኝ ካለ ለሚቀጥለው ችሎት የማቅረብ መብት እንዳላቸው ገልጻል። ይሁን እንጂ ተጠርጣሪው በምን ወንጀል ተጠርጥሬ እንደተያዝኩ አላውቅም ብለው ያቀረቡትን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል። ከዚህ በፊት በነበሩ የችሎት ቀናትም እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ቀርቦ አያቅም ያለው ችሎቱ ለእያንዳነዱ ተጠርጣሪ በምን ጉዳይ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ መገለፁንም አስታውሷል። በሰብኣዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት በነጎሀ አጽብሃ መዝገብ ሥር የሚገኙ ተከሳሶች በራሳቸውና በጠበቆቻቸው የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል። በተጠርጣሪ ጠበቆች በኩል እንደመከራከሪያ አድርገው ሲያነሱት ከነበረው ጉዳይ መካከልም የወንጀለኛ ሥነ ስርዓት ሕጉ በማይፈቅደው ሁኔታ ዐቃቤ ሕግ የመርማሪ ፖሊስን ሥራ እየሠራ ነው የሚገኘው የቀዳሚ ምርመራ ሥራም ከጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ተለይቶ መታየት አለበት የሚሉና መሰል ሕጋዊ ጥያቄዎችን ለችሎቱ አሰምተዋል።

በሌላ በኩል ላለፉት ወራት መርማሪ ፖሊስ “የምስክሮችን ቃል እያዳመጥኩ ነው፤ የህክምና ማስረጃዎችን እየሰበሰብኩ ነው” የሚሉና ሌሎች ምክንያቶችን እያቀረበ ነው ያሉት ጠበቆች ለመርማሪ ፖሊስም ሆነ ለዐቃቤ ሕግ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዳይፈቀድላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል። መርማሪ ፖሊስና ዐቃቤ ሕግ በበኩላቸው ከወንጀሉ ሥፋትና ውስብስብነት አንጻር የምጠይቃቸው ጊዜዎች ብዙ አይደሉም መረጃዎች ባልተሰባሰቡበት ሁኔታም ክስ መመስረት ስለማይቻል ችሎቱ የተጠርጣሪ ጠበቆች ያነሱትን መከራከሪያ ውድቅ እንዲያረገው ጠይቀዋል። በኹለቱም ወገን ያለውን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱ የ12 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለጥር 27 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on February 2, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 2, 2019 @ 12:36 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar