www.maledatimes.com በእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በአስቸኳይ ማክተም አለበት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በአስቸኳይ ማክተም አለበት

By   /   November 1, 2012  /   Comments Off on በእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በአስቸኳይ ማክተም አለበት

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 53 Second

1
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP)
(ዴሞክራሲያዊ/Democratic)
ጥቅምት ፲፰ ቀን ፪ ሺህ ፭ ዓ. ም
October 28, 2012

የአምባገነን መንግሥት መገለጫ ባህሪያቱ ከዕለት ዕለት ጉልህ እየሆኑ ሲመጡ መሻሻል ወይም መለወጥ ከቶውንም አይጠበቅበትም። በመሆኑም ነው በደቡብ ወሎ፤ በደጋን እና በገርባ ከተሞች በእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ ጥቅምት 11 ቀን 2005 ዓ. ም  (October 21, 2012) የተፈፀመው ግድያ፤ ድብደባና እስራት የህወሓት/ኢህአዴግን ፀረ-ሕዝብ ባህሪና አምባገነናዊነት መልሶ ያረጋገጠው። የአካባቢው የእስልምና ሃይማኖት
ተከታዮች ገርባ ከተማ ለጸሎት በተሰባሰቡበት ሰዓት የፀጥታ ኃይሎች በበርካታ ወገኖቻችን ላይ የግፍ እርምጃ በመውሰድ ሞት፤ መቁሰል፤ መደብደብንና መፈናቀልን አድርሰዋል።
ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ይህንን ኢ-ሰብዓዊ የዕብሪት እርምጃ በጥብቅ ያወግዛል።የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን የዕምነት መብታቸውን ለማስከበር፤ህወሓት/ኢህአዴግ እመራበታለሁ የሚለውን ሕገ-መንግሥት አክብረው፤ የመጅሊስ ምርጫና ዕምነታቸውን በነፃነት ለማስፋፋት በሚያደርጉት ሰላማዊ ትግል ህወሓት/ኢህአዴግ ጣልቃገብነቱንና ለጭፍጨፋ ሰበብ ፍለጋ የሚያደርገውንም ትንኮሳ ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) በጥብቅ ይቃወማል። ወገኖቻችን በህወሓት/ኢህአዴግ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 27 ውስጥ ተፈቅዷል ከተባለው መብት አልፈው የፈጸሙት ህገ-ወጥ ተግባር ሳይኖር፤ የመንግሥትን ጣልቃገብነት ስለተቃወሙ ብቻ ማሳደድ፤ ማሰር፤መደብደብና መግደል የአምባገነኑን መንግሥት ግፈኛነት በግልጽ ከማሳየቱም በላይ በአፋኝ አገዛዙ የመቀጠል ፍላጎቱንም ያረጋግጣል።
850 Sligo Avenue Suite # 8 P.O.Box 8141 P.O.Box 88675 Siver Spring , MD 20910 Silver Spring, MD 20910 Los Angeles, CA 90009
Phone: 301-578-4466 Fax: 301-449-8363 Email Address: eprp-democratic@eprp-ihapa.com2 ሁሉን ባስደነቀ መልኩ ወገኖቻችን ከአሥር ወራት በላይ ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ
ላነሷቸው የመብት ጥያቄዎች አግባብ ያለው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ሰላማዊውን ትግል ፈር ለማሳት በተቀነባበረ መንገድ “ሠላምን እንደ ፍርሃት፣ ዝምታንም እንደ ሽንፈት” የሚያየው ዕብሪተኛው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ሰላማዊ ምዕመናኑን በመካነ-መስጂዳቸው ውስጥ እየገባ መግደልንና ማቁሰልን መረጠ። የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን የህወሓት/ኢህአዴግን ትንኮሳ አክሽፋችሁ በሰላማዊ መንገድ የዕምነት መብታችሁን ለማስከበር በምታደርጉት ትግል ላይ ኢሕአፓ (ዴሞክራሲዊ) ምንጊዜም ከጎናችሁ እንደሚቆም ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል።
ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕምነት ፓትሪያርክ እስከመምረጥና ቀኖናን እስከማሻር ጣልቃ በመግባት፤ በቅርቡ ደግሞ ገዳማትን በመድፈርና መነኮሳትን በማሳደድ እየፈፀመ ካለው አሳፋሪ ተግባራቱ መታቀብ አለበት እንዳልነው ሁሉ አሁንም በቤተክርስትያን ተቋማት ውስጥ ጣልቃ ገብነቱ በአስቸኳይ ማቆም አለበት እንላለን። የክርስትናና የሌሎች ዕምነት ተከታዮች ሁሉ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ኢትዮጵያውያንን በብሄረሰብ ከፋፍሎና አቃርኖ ለማፋጀት እንደሞከረው፤አሁንም በሃይማኖት ሊከፋፍልና ሊያጋጭ እየጣረ መሆኑን ልናስተውል ይገባል።
የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን በሚያደርጉት ትግል ላይ እንደታየው  ህወሓት/ኢህአዴግ በሕዝቡ ውስጥ ጥርጣሬና ጥላቻ እንዲኖር እያደረገ ያለውን ጥረት በሀገራዊ የአንድነት ስሜት በመገንዘብ፤ ከእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ጎን በመቆምና በመታገል የህወሓት/ኢህአዴግን ተንኮልና ደባ ልናከሽፍበት ይገባል እንላለን።
በተለያዩ ወቅቶች ክርስቲያን ወገኖቻችን ያነሷቸው ጥያቄዎችም ተመሳሳይ የዕምነት ነፃነት ጥያቄዎች ነበሩ፤ አሁንም ናቸው። የክርስትናም ሆነ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ያነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢ ናቸውና ትክክለኛ ምላሽ ያገኙ ዘንድ የኢትዮጵያውያን ሁሉ የተባብረ የትግል አንድነት ያለጥርጥር አስፈላጊ ነው። ስለዚህ እጅ ለእጅ ተያይዘን በመታገል የጋራ በሆነችው ሀገራችን ውስጥ መብቶቻችንን ልናስከብር ይገባል እንላለን!!
የዕምነት ነፃነት መብታቸው እንዲከበር በመጠየቃቸው የታሠሩት ይፈቱ!!
በኢትዮጵያውያን የጋራ ትግል የዕምነትና ሌሎች መብቶቻችንንም እንቀዳጃለን!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 1, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 1, 2012 @ 10:39 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar