www.maledatimes.com በሃገራችን ሰላም እና በአንድነታችን ላይ ሰላምን የሚያድናቅፉ አካላት ላይ የመረረ እርምጃ እንወስዳለን ። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሃገራችን ሰላም እና በአንድነታችን ላይ ሰላምን የሚያድናቅፉ አካላት ላይ የመረረ እርምጃ እንወስዳለን ። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ

By   /   February 3, 2019  /   Comments Off on በሃገራችን ሰላም እና በአንድነታችን ላይ ሰላምን የሚያድናቅፉ አካላት ላይ የመረረ እርምጃ እንወስዳለን ። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 12 Second

  1. ‹ሰላማችንንና አንድነታችንን በሚያደናቅፉ ላይ የትዕግሥታችንን ያህል የመረረ ዕርምጃ እንደምንወስድ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ››

‹‹ሰላማችንንና አንድነታችንን በሚያደናቅፉ ላይ የትዕግሥታችንን ያህል የመረረ ዕርምጃ እንደምንወስድ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ››
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ዓርብ ጥር 24 ቀን 2011 ዓ.ም. በፓርላማ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት ፓርላማ ሲደርሱ በአፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ አቀባበል ሲደረግላቸው

‹‹ሰላማችንንና አንድነታችንን በሚያደናቅፉ ላይ የትዕግሥታችንን ያህል የመረረ ዕርምጃ እንደምንወስድ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ››

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ዓርብ ጥር 24 ቀን 2011 ዓ.ም. በምክር ቤቱ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች ቢስተዋሉም መንግሥታቸው መታገስን እንደመረጠ፣ ነገር ግን የአገሪቱን ሰላምና አንድነት ለማደናቀፍ የሚደረግ ሙከራን መንግሥታቸው እንደማይታገስ በመግለጽ ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጡ።

የምክር ቤቱ አባላት በርከት ያሉ ጥያቄዎችን በሁለት ዙር አቅርበዋል፡፡ በመጀመርያው ዙር ወቅታዊ የአገሪቱን ሁኔታ በተለይም በበርካታ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን፣ የነዋሪዎች መፈናቀልን፣ በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በመንግሥት ጥሪ ተደርጎላቸው ወደ አገር የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሉበትን ሁኔታ፣ እንዲሁም መንግሥት የጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥ ባለመቀበል ለማደናቀፍ የሚሠሩና ለሕግ ተገዥ ያልሆኑ ተጠርጣሪዎችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን በማቅረብ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት መንግሥት ችግሮቹን ለመቅረፍና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ምን እያደረገ እንደሆነ ማብራርያ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራርያ መንግሥት ሆደ ሰፊ፣ አርቆ አሳቢና ችግሮችን በብስለት ለመፍታት መምረጡን፣ ይህ ካልሆነ ዴሞክራሲን በቀላሉ ለማምጣት የሚቸግር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት በማስመልከት፣ እንዲሁም ከውጭ የገቡ ጥቂት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያልተገባ እንቅስቃሴ መንግሥታቸው በትዕግሥት የሚያልፈውም ለዚህ እንደሆነ አስረድተዋል። ሃያ የሚጠጉ የታጠቁም ያልታጠቁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር እንደተመለሱ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ወደ አገር እንዲመለሱ ለሁሉም የቀረበው የሰላም ጥሪ አንድ ዓይነት እንደሆነና ይህም የሰላም መርህን የተከተለ ብቻ እንደነበር አስረድተዋል። በመሆኑም ከአንድ ፓርቲ ጋር የተለየ፣ ከሌላው ጋር የተለየ ድርድር አለመደረጉን፣ እንደዚህ የሚያደርግ መንግሥት ሊኖር እንደማይችል ገልጸዋል።

ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ ውስጥ ግማሾቹ የዴሞክራሲን መርህ ተከትለውና አክብረው ለአገራቸውና ለሕዝባቸው የሚታገሉ እንዳሉ፣ በሌላ በኩል በሰፊው የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ገብተው የሐሳብ ልዕልና ለማምጣት የተቸገሩ ደካማ የፖለቲካ ፓርቲዎችም እንዳሉም የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኃይልን አማራጭ አድርገው የተሠለፉና ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨትና አገሪቱን ለማተራመስ የሚሠሩ መኖራቸውንም አስረድተዋል፡፡

ዴሞክራሲን ለማደላደል ሲባል መንግሥት ትዕግሥት ማድረጉን እንደሚቀጥል፣ ነገር ግን በሕዝብ ዘንድ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር የአገሪቱን አንድነት ለመረበሽ፣ እንዲሁም የአገሪቱን ሰላምና ዴሞክራሲ አደጋ ላይ የሚጥል ያልተገባ ተግባር በሚፈጽሙት ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።

‹‹ሰላማችንንና አንድነታችንን በሚያደናቅፉ ላይ የትዕግሥታችንን ያህል የመረረ ዕርምጃ እንደምንወስድ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፤›› ብለዋል።

በሕግ የሚፈለጉ ነገር ግን በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ግለሰቦችን በሚመለከት በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሠርቶ ወንጀለኛ መሆኑን መንግሥት ካወጀ በኋላ ያልታሰረ ግለሰብ የለም፡፡ ልዩነቱ መንግሥት ቀለብ እያቀረበለት እስር ቤት መሆኑና ራሱን ማሰሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡

መንግሥት በተለይም የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈጸም በዋናነት የጠረጠራቸው የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣቱን፣ ነገር ግን በትግራይ ክልል ተሸሽገው እንደሚገኙና ክልሉም እንዳልተባበረ መግለጹ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የሰጡት ምላሽ አቶ ጌታቸው አሰፋንና ሌሎች ያልተያዙ ግለሰቦችን የሚመለከት ቢሆንም፣ እሳቸው ግን በቀጥታ እነዚህን ተፈላጊዎች በስም አልጠቀሱም።

 ‹‹በእኔ እምነት ሁሉም ታስሯል፡፡ እንዲያውም በመንግሥት እስር ቤት የታሰሩ ግለሰቦች ቤተሰባቸው እየጠየቃቸው ስፖርት እየሠሩ ነው ያሉት፡፡ ራሳቸውን ያሰሩ ግን ይኼንንም ዕድል አላገኙም፡፡ የጊዜ ነገር እንጂ ወንጀል ሠርቶ ተሸሽጎ የሚቀር የለም፤›› በማለት አስተያየታቸውን በገለጹበት ወቅት ምክር ቤቱ በአባላቱ የሳቅ ድምፅ ተሞልቷል፡፡

ማንኛውም ዜጋ በአገር ውስጥ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋውሮ የመሥራትና የመኖር መብቱ ሊነፈግ እንደማይገባ በአፅንኦት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለው ዜጎችን የማፈናቀል ድርጊትን አውግዘዋል።

 ‹‹ክልል ወሰን እንጂ ሉዓላዊ ድንበር፤›› አይደለም ሲሉም አሳስበዋል።

የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በተመለከተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ከሰጧቸው ምላሾች አንዱ ታላቁ የህዳሴ ግድብን የሚመለከት ሲሆን፣ በቀጣይ አራት ዓመታት ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

ስንዴ ከውጭ እያስገቡ መቀጠል እንደማይቻል የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይኼንን ችግር ለመቅሰፍ ከፍተኛ ትኩረት ለግብርናው ዘርፍ መሰጠቱን በመግለጽ በተለይም የመስኖ ግብርናን ማስፋፋት የግድ እንደሚል አመልክተዋል።

በአገሪቱ የተፈጠረውን ተስፋ ሰጪ ለውጥ የውጭ አጋሮች በከፍተኛ ደረጃ እየደገፉ እንደሚገኙ፣ በተለይም በኢኮኖሚው መቀዛቀዝ ለውጡ እንዳይደናቀፍ የዓለም ባንክ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት የሚያስችል 1.7 ቢሊዮን ዶላር የቀጥታ በጀት ድጋፍ ከአሥራ አምስት ዓመታት በኋላ ማድረጉን አስረድተዋል።

 የሚዲያ ነፃነትን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ሚናቸውን በአግባቡ የሚወጡ ሚዲያዎች እንዳሉ ሁሉ፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት የሚቸገሩና አጀንዳ እየተቀረፀላቸው ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ መኖራቸውን አስታውቀዋል።

መገናኛ ብዙኃን ሚናቸውን በሚዛናዊነትና በተዓማኒነት በመወጣት ለማኅበረሰቡ ፋይዳ ማበርከት እንዲችሉ፣ ያለባቸውን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on February 3, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 3, 2019 @ 2:36 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar