www.maledatimes.com በ117 ሚሊዮን ብር ወጪ 7 በመቶው የአዲስ አበባ አስፋልት ቀለም ሊቀባ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በ117 ሚሊዮን ብር ወጪ 7 በመቶው የአዲስ አበባ አስፋልት ቀለም ሊቀባ ነው

By   /   February 5, 2019  /   Comments Off on በ117 ሚሊዮን ብር ወጪ 7 በመቶው የአዲስ አበባ አስፋልት ቀለም ሊቀባ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second

በአዲስ አበባ ከተማ 200 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ የመንገድ ላይ ስርዓት ማስያዣ ምልክቶችን ቀለም የመቀባት ሥራ በ117 ሚሊዮን ብር ወጪ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ። ይሁንና ኤጀንሲው የመንገድ ቀለሙ አጠቃላይ ከሚያስወጣው ወጪ መንግሥት ያፀደቀው 52 ሚሊዮን ብር መሆኑንም ጨምሮ ገልጿ።

ታኅሣሥ 2012 ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የመንገድ መቀባቱ፥ የመንገድ ስርዓት ማስያዣ ሕጎች ለኅብረተሰቡ አንድ ዓይነት መልዕክት የሚያስተላልፉ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ ዘመናዊ ግብዓቶችን እንደሚጠቀም ይታመናል። በመሆኑም እነዚህን ዘመናዊ ቀለሞች ለመጠቀም የአገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል ተብሏል።

እስካሁን በጥቅም ላይ የዋሉት የነበሩትን ፈሳሽ እና ትሪሞ ፕላስቲክ የሚባሉ ሲሆኑ ከ6 ወር እስከ አንድ ዓመት የሚያገለግሉ ናቸው። ይህንን ችግር ለመፍታት ኤጀንሲው አሁን የሚጠቀምባቸው ዘመናዊ ኮልድ ፕላስቲክ እና ፕሪማርክ ፕላስቲክ የሚባሉ የቀለም ዓይነቶች ሲሆኑ እስከ 2 ዓመታት እንደሚያገለግሉ ታውቋል።
የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም የእገረኛ ማቋረጫ መንገዶቸን እንዲሁም የትራፊክ መብራት ተከላዎች የሠራ ሲሆን የትራፊክ መብራት ተከላዎችም በተለያዩ አካባቢዎች እየተከለ ይገኛሉ። እስከአሁን 17 አካበቢዎች ተከላውን የተደረገ ሲሆን ተጨማሪ 8 አካባቢዎችን በዚሁ ዓመት ሠርቶ እንደሚጨርስ ኤጀንሲው አስታውቋል።

አዲስ አበባ ከተማ 6 ሺሕ 573 ኪ.ሜ የመንገድ ኔትወርክ ባለቤት ስትሆን የመንገዶቿን ሁኔታ ስንመለከትም 2 ሺሕ 763 ኪ.ሜ በአስፋልት ደረጃ፣ 1 ሺሕ 675 በጠጠር ደረጃ፣ 2 ሺሕ 135 በኮብልስቶን ደንጋይ ንጣፍ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በዚህ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ላይ ስርዓት ማስያዣ ምልክቶች የሚቀባው ከጠቅላላው 7% ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on February 5, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 5, 2019 @ 3:13 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar