በኢትዮጵያ ለእረጅም ዘመናት ለምግብነት የሚጠቀሙበት የእል ዘር ጤፍ በሆላንዳውያን ባለሃብቶች የባለቤትነት የስም ውርስ ተወርሶ የእኛ ነው በማለት ላለፉት አስራ ስምንት አመታት በጤፍ ዘር ላይ መጠነ ሰፊ እና ከፍተኛ የሆነ የጤፍ ዝርያን በባለቤትነት ሲቆጣጠሩ ቆይተው ብዙ ቢሊዮን ዶላርስ ገንዘብ ያመረቱት እነዚሁ ሆላንዳውያን የባለቤትነቱን ይገባኛል ጥያቄ ኢትዮጵያ ቀድማ ብታቀርብም ሰሚ አልባ በሆነ መንግስት ምንም አይነት ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶአል ።
አሁን ባለው አዲሱ የኢትዮጵያ አስተዳደራዊ መንግስት የባለቤትነት ጥያቄው እና ጤፍ የተሰኘው እህል ከእረጅም ዘመናት ጀምሮ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቧ እንደሆነ እና ቀደም ብሎ የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያውያኖች የፈረስ ምግብ ነው የሚመገቡት ሲሉ የነበረውን ይህንን እህል ዛሬ ከፍተኛ ንጥረ ነገር እንዳለው በማወቃቸው የንብረትነት እና እንዲሁም እህሉን ወደ ተለያዩ የምግብ አይነቶች በመቀየር ለአለም አቀፉ የምግብ ጥራት እና ደረጃ በማቅረብ የተለያዩ ማፍኖችን ዶናት እና ኬኮችን አቅርበው ለታላላቅ የፊልም ባለሙያዎች የሰውነት መጠበቂያ ኑትሬሽን የሚያገኙበት የምግብ አይነት መሆኑን አሳውቀዋል ።
ይህ በንዲህ እንዳለ ታዲያ የኢትዮጵያ የይገባኛል ጥያቂ ተገቢው እና መሰረታዊውን ምላሽ ማግኘት ያለበት በአለም አቀፍ የኮፒራይት ህግ መሰረት ዘሩ የመጣው ከምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን በአሁን ሰአት በአይዳኦ ሰሜን አሜሪካ እና በአውሮጳ የተወሰኑ ሃገራቶች እንዲበቅል መደረጉ ይታወሳል ;ይህንን ተከትሎ መንግስት የባለቤትነት ጥያቄውን እና ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅማ ጥቅም እንደ ኢትዮጵያ ቡና በከፍተኛ ደረጃ ማስጠበቅ አለበት ሲሉ ህዝቦች ይመክራሉ ።
የጤፍን ባለቤትነት በተመለከተ በአንድ ሆላንዳዊ ዜጋና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ሲካሄድ የነበረው የይገባኛል ክርክር ወደ ኢትዮጵያ እያደላ ነው። ዘሄግ ሆላንድ የተሰየመው ችሎት ቀደም ብሎ ባለቤትነቱን በስሙ አስመዝግቦ ከነበረው ኔዘርላንዳዊ መቀማቱን አቶ ፍፁም አረጋ አረጋግጠዋል። በቀጣይ ግለሰቡ ይግባኝ የሚጠይቅ ከሆነ ጉዳዩ በድጋሜ ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ይተላለፋል። ሲል ጴጥሮስ አሸናፊ የጻፈውም አጭር የአማርኛ ጽሁፍ እዚህ ላይ ሰፍሯል።
Average Rating