የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ሃውልት በአፍሪካ ዩኒየን መተከሉን ምንጮቻችን ጠቆሙ ። የአፍሪካ አባት ከሚባሉት ውስጥ መስራቾቹ የግንባር ቀደምትነትን ሚና ከተጫወቱት ውስጥ መካከል ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ፣የጋናው ክዋሜ ንክሩማህ ፣ የኬንያ ጆሞ ኬንያታ ፣የግብጹ ጀማል አብዱል ናስር እና ሌሎችም ታላላቅ የአፍሪካ ህብረት መስራቾች በሙሉ ትልቅ አሉታዊ ተጽእኖ ለአፍሪካ ማሳደራቸው ይታወሳል ፡፤
በተለይም በአፍሪካ የነጻነትን ነጸብራቅ ለመፈንጠቅ ትልቅ ተጋድሎ ያደረጉት የአፍሪካ መሪዎች ውስጥ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ እስከ ኤዥያ ድረስ የነጻነት ትግል በማድረግ አውራ እንደነበሩ ይታወቃል። ሃይለስላሴ በባርነት ለወደቁ የአፍሪካ ሃገራት ትልቅ የነጻነት አርማ ሆነው የቆዩ እና ሃገራቶቹ የእራሳቸውን ነጻነት አውጀው የሚኖሩበትን ትልቅ ስትራቴጂ ሲነድፉ እና ሲወያዩ የነበሩ ትልቅ ንጉሰ ነገስት እንደነበሩ ታላላቅ ባላባቶች ይናገራሉ ።
ከዚህም ባሻገር ቀዳማዊ ሃይለ ከንግስት ኤልሳቤጥ ጋር በነበራቸው የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው በመሆኑ ለአፍሪካ ነጻነት ትልቁን ለውጥ አምጥተዋል ይባልላቸዋል። በአለም አቀፍ ከፍተኛ ጫና ከሚያሳድሩ ሰዎች ቅድሚያ ተርታውን የሚይዙት ሃይለ ስላሴ በአፍሪካ የባርነት ቀንበርን ተሸክመው የነበሩትን አገሮች ለምሳሌ አንጎላ፣ሞዛምቢክ ሮህዴሲያ ወይንም የአሁኑ ስሟ ዝምባብዌ፣ ናምቢያ እና ደቡብ አፍሪካ በመካከለኛው የውጭ የግዥ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛውን ስፍራ ሲይዙ በዚህ ሁኔታ ነጻነታቸው እስከተከበረበት እለት ድረስ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛውን ጫና አሳድሯል;
የመጀመሪያውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ሰላሳ አንድ ሃገራት መሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴም ከፍተኛ እና ጉልህ ሚና ነበረው ከእነዚህም መካከል የአፍሪካ በመተባበር መስራት አለባቸው ብለው ከሚያምኑት ውስጥ ክዋሜ ንክሩማህ ቀዳሚ ሲሆኑ የአፍሪካን ናሽናሊዝም እና ኮሚቴ በፓን አፍሪካኒዝም አባት በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ።
በ፲፱፶፪ አካባቢ የተመሰረተው አፍሪካ ህብረት ቋሚ እና ዋና መስሪያቤቱ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሲሆን ሌሎች አመታዊ ስብሰባዎችን በተለያዩ ሃገራት ለጊዜያዊ መፍትሄ መስጫ ውይይት እንደሚያደርግ ቢታወቅም በዋነኝነት የሚታወቀው የአዲስ አበባ ዋና መስሪያቤት እንደነበር ይታወሳል።
ከእረጅም ዘመናት በኋላ ለቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ እርሳቸው እና ሌሎች ባልደረቦቻቸው በጋራ ባስገነቡት የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ህንጻ በር ላይ መታሰቢያ ሃውልታቸው እንዲቆም በመወሰኑ በዚህ ሳምንት ሊተከል ችሏል። ታላላቅ የአለም አቀፍ ባለስልጣናቶች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የስደተኞች ኮሚሽን ዋና ሃላፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በቦታው ለመገኘት ከስዊዘር ላንድ ወደ ኢትዮጵያ ማቅናቱም ተገልጧል።
Average Rating