www.maledatimes.com በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ከጥር 24 ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እየደረሰ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ከጥር 24 ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እየደረሰ ነው

By   /   February 8, 2019  /   Comments Off on በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ከጥር 24 ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እየደረሰ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 10 Second

በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ከጥር 24 ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት ለበርካታ ሰዎች ሞትና ለንብረት ውድመት ምክንያት መሆኑን የአማራ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡

በተለይ የ24ኛ ክፍለ ጦር በ33ኛ ክፍለ ጦር በሚተካበት ወቅት በአካባቢው የተሰማሩ ፅንፈኛ ኃይሎች አጋጣሚውን በመጠቀም ባስነሱት ግጭት ከበርካታ ሰዎች ሞት በተጨማሪ ቤቶችም ተቃጥለዋል ብሏል ክልሉ፡፡በዚም የተነሳ ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው የአካባው ነዋሪ ከቀየው መፈናቀሉን የአማራ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኻኝ አስረስ በተለይ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

ከጎንደር ወደ አርማጭኾ የሚወስደው ምስራቅ ደንቢያ የትራስፖርት ሂደቱ እየተስተጓጎለ መሆኑንና በዛሬው ዕለት በአካባቢው ሰርገው የገቡ ፅንፈኛ ኃይሎቹ ሰዎችን ጠልፈው እስከመውሰድ መድረሳቸውንም አቶ አሰማኻኝ ተናግረዋል፡፡
በየቀኑ እየደረሰ ያለው ጥፋት የአደጋውን መጠንና የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ አስቸጋሪ እንዳደረገውም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው ለደረሰው ዝርፊያና ወንጀሎች ቡድኖቹ በተደራጀ ሁኔታ መፈፀማቸውንም ክልሉ ገልጿል፡፡

በክልሉ ከተመዘገበው 80ሺህ ተፈናቃይ ውስጥ 39ሺህ ያህሉ ከዚህ ቀደም በማዕከላዊ ጎንደር በተፈጠረ ግጭት ቀያቸውን ጥለው የተሰደዱ ናቸው፡፡

Image may contain: 1 person, sitting and suit

የክልሉ መንግስት ፀጥታውን ለማስከበር እየሰራ ቢሆንም በወንጀሉ ላይ የተሰማሩት ቡድኖች በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ ሰርገው በመግባታቸው ሂደቱን አስቸጋሪ እንዳደረገው ክልሉ ገልጿል፡፡ጉዳዩ በክልሉ መንግስት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ ወንጀለኞችን በማጋለጥና የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን በመጠቆም አካባቢውን ወደ ቀደመ ሰላም ለመመለስ ጥረት መደረግ አለበትም ተብሏል፡፡

የአማራ ክልል በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠር የፌደራል መንግስት መከላከያን ጨምሮ ትብብር እንዲያደርግም ጠይቋል፡፡ይህ ካልሆነ ግን ችግሩ እየሰፋ በአካባቢው የሚደርሰውን ውድመትና ጥፋት ክፉኛ እንደሚያባብሰው የክልሉ መንግስት ኮሙኑኬሽን አቶ አሰማኻኝ አስረስ ተናግረዋል፡፡

ግጭቱ በአማራና በቅማንት ህዝቦች መሃል ሳይሆን በሶስተኛ ወገን ተልዕኮ የተሰጣቸው ቡድኖች እየፈጠሩት ያለ ችግር መሆኑንም አቶ አሰማኻኝ ለኢቢሲ ገልፀዋል፡፡

በስመኘው ይርዳው

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on February 8, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 8, 2019 @ 12:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar