በሰሞኑ ከፍተኛ የሆነ ውጥረትን እና ምስላቸውን አይመስልም ተብሎ ተቃውሞ የቀረበበት የቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ የመታሰቢያ ሃውልት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ መቆሙን እና የምርቃት ስነ ስርአቱ በዛሬው እለት በቅጥር ግቢው መከናወኑን ተገልጧል ።
ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ከኢትዮጵያ አልፈው ለአፍሪካ ያደረጉት አስተዋጾ የበረታ ከመሆኑም በላይ ለመላው አፍሪካ ኩራት መሆናቸው ይታወሳል ። ሆኖም ላለፉት ሃያሰባት አመታት በትግራይ ወይንም ህወሃት አገዛዝ ስር ኢትዮጵያ በወደቀችበት ዘመን ማንኛውንም መልካም ስራቸውንም ለማስታወስም ሆነ ጥሩ ነገር የሰሩ የኢትዮጵያ ታላላቅ ሰዎች ሊዘከሩ እንዳልቻሉ ይታወሳል ። ከምንም በላይ የጥቁር ህዝቦች ድል የሆነውን የአድውዋንም ድል ለማስታወስ እንኳን በከባድ ቀውስ ውስጥ የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ ወደ ቀድሞዋ የኢትዮጵያ ትቅደም መሰረት የተጓዘች ይመስላል። የወያኔ ህወሃት ውድቀት የሁሉንም የኢትዮጵያን መሰረታዊ ድንጋይ የተጣለበትን ሁሉ እንዲነሳ አድርጎታል።
በቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የቀዳማዊ ለአፍሪካ አንድነት ምስረታ ብሎም መቀመጫው ኢትዮጵያ አዲስ አበባ እንዲሆን ዋጋ ከፍለዋል ከሚባሉት ታላላቅ የሃገሪቱ መሪዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ወይንም ጥቂቶቹ ብርቱ የሀገራችን ዲፕሎማቶች ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ፣ ከተማ ይፍሩና
ዶክተር ምናሴ ታሪክ ሁልጊዜም ይዘክራቸዋል ።
እንደ ምሳሌ ያህል ከአምባሳደሮቻችን ውስጥ ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ በኢትዮጵያ ውስጥ ከጣሉት ትልልቅ የስራ አሻራቸው ውስጥ ጥቂቶቹ ኤርትራን በኮንፌዴሬሽን ማዋሀድ፤ ኦጋዴንን ከእንግሊስ በዲፕሎማሲ ማስመለስ፤ ኢትዮጵያ የUN አባል እንድትሆን ማድረግ፤ ጣልያን በወረረን ጊዜ ትላልቅ ዲፕሎማሲ በማድረግ የኢትዮጵያን ሉዋላዊነት በማስገንዘብ
በጠቅላይ ሚንስትር እና በሌሎች አፍሪካን መሪዎች የተመረቀው ይሄው ሃውልት የስራቸውን መዘከሪያ እንደሚሆን እና በሃገራችን ላይ በጣሉት ከፍተኛ አሻራ መታሰቢያ እንደሚሆን ተገልጧል። ይህንን ሃውልት በአጭር ጊዜ የሰሩት መስፍን ተስፋዬ፣ ረዳት ፕሮፌሰር መኮንን እና ሄኖክ አዘነ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን የህወሃት የሃይለስላሴ ሃውልት በአደባባይ አይቆምም ብሎ አምጾበት የነበረው ህልሙ እዚህ ጋር እንዲቀበር ተደርጓል።
በሌላም በኩል የሃይለስላሴ መታሰቢያ ማህበር ምስጋናውን ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በመግለጫው አመልክቷል። ከስር አያይዘነዋል ይመልከቱ ። ማለዳ ታይምስ ሚዲያ
Average Rating