www.maledatimes.com የየካ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የ18 ሚሊዮን ብር የሕንፃ ኪራይ ጥያቄ አስነሳ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የየካ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የ18 ሚሊዮን ብር የሕንፃ ኪራይ ጥያቄ አስነሳ

By   /   February 10, 2019  /   Comments Off on የየካ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የ18 ሚሊዮን ብር የሕንፃ ኪራይ ጥያቄ አስነሳ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 23 Second

በየካ ክፍለ ከተማ ሥር የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ ቀድሞ በዓመት አምስት ሚሊዮን ብር እየከፈለበት ካለው ሕንፃ በመልቀቅ በዓመት 18 ሚሊዮን ብር ወደሚከፈልበት ሕንፃ ለመዘዋወር የኪራይ ውል መፈጸሙ ጥያቄ ተነሳበት፡፡

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቢሮው ሠራተኞች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ፊት ለፊት የሚገኘው የየካ ክፍለ ከተማ የአነስተኛ ግብር ከፋዮች ጽሕፈት ቤት አዲስ ሕንፃ ተከራይቷል፡፡ በተጋነነ ዋጋ መገናኛ አካባቢ ግንባታው ወዳልተጠናቀቀ አዲስ ሕንፃ፣ ከየካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለመዘዋወር ውል መግባቱን ገልጸዋል፡፡ ሠራተኞቹ እንደገለጹት ወደ አዲሱ ሕንፃ ለመዘዋወር ስምምነት ቢፈጽምም፣ የሕንፃው ግንባታ ባለመጠናቀቁ በዕለቱ ሊዘዋወር አልቻለም ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱን በነባሩ ሕንፃ ለአንድ ወር እንዲቆይና ተጨማሪ ወጪ እንዲያወጣ አድርጎታል ብለዋል፡፡

ምንም እንኳ ጽሕፈት ቤቱ የየካ ግብር ከፋዮች የሚስተናግዱበት ቢሆንም፣ ሕንፃው የሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ በመሆኑ ወደ ራሱ ክፍለ ከተማ እንዲዘዋወር ከቦሌ ክፍለ ከተማ ግፊት እንደነበረበት ተጠቅሷል፡፡

ከዋጋ ግነቱ በተጨማሪ በአንድ ጊዜ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ማስተናገድ ከሚችል ሥፍራ፣ ለምን ወደ አነስተኛ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ ወዳለው ሕንፃ ማዘዋወር አስፈለገ የሚል ጥያቄም አስነስቷል፡፡

የጽሕፈት ቤቱን አዲስ ሕንፃ ኪራይ በተመለከተ ውል መፈረሙን ለሪፖርተር ያረጋገጡት የክፍለ ከተማው ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ አዳነ ገብረ እግዚአብሔር፣ የኪራይ ስምምነቱ በአስተዳደሩ የፋይናንስ ቢሮ ዕውቅና መሠረት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱን ማዘዋወር ያስፈለገበት ምክንያት ነባሩ ሕንፃ ለቢሮ ሠራተኞች ጠባብ ከመሆኑም በላይ፣ ለግብር ከፋዮችም አመቺ ባለመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ዞሮ ዞሮ ለተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ሲባል ነው፤›› ያሉት አቶ አዳነ፣ ‹‹ግብር ከፋዮቻችን የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በመሆናቸው ብዙ ሳይርቅ በራሳቸው ክፍለ ከተማ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ነው፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

ውሉ የተፈረመው ከየካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ስለሆነ በዕለቱ እንዳልተዘዋወረ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ የአዲሱ ሕንፃ የኤሌክትሪክና የኔትወርክ ዝርጋታ ስላልተጠናቀቀ እስከ የካቲት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በነባሩ ሕንፃ ለመቆየት መወሰኑን አስረድተዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on February 10, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 10, 2019 @ 12:03 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar